Get Mystery Box with random crypto!

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች የምትገባ መሆኑን | Fano Media Network

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች የምትገባ መሆኑን በአክብሮት እያሳወቅን ይህንንም ድርጊት ተከታትሎ የሚያሳውቅ እና የሚያስፈጽም የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደሥራ እንዲገባ የሚደረግም መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡

በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት የሊቀ ሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር በመምጣት ህይወቱን ላጣው ልጃችን እግዚአብሔር ነፍሱን በአብርሃም፣ በያዕቆብና በይስሐቅ እቅፍ ያኑር፣ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ያድልልን እያልን ቀላልም ሆነ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ የቤተ ክርስቲን የጭንቅ ቀን ልጆች ደማችሁን እና መከራችሁን እንደ ሰማእታት ዋጋ ይቆጥርላችሁ ዘንድ ጸሎታችን ነው፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

https://t.me/GeezMediaCenter
https://t.me/GeezMediaCenter
https://t.me/GeezMediaCenter