Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለግሬዶች A የሩቅ ሀገር ሰው ነሽ እንዴት ነሽ ዘመዴ፤ ኧረ ተይ ጠይቂኝ ብቅ ብለሽ አንዳን | 🌿መርጌታ🌿 ጋሻየ 🌿የበሀል መድሀኒት🌿 አዋቂና 🌿ቀማሚ

ይድረስ ለግሬዶች
A
የሩቅ ሀገር ሰው ነሽ እንዴት ነሽ ዘመዴ፤
ኧረ ተይ ጠይቂኝ ብቅ ብለሽ አንዳንዴ።
አንቺ ኩሩ ዘመድ የኔ ዘመናይ፤
እንደ እንደ አደይ አበባ በአመት አንድ ጊዜ ብቅ አትይም ወይ።
ሀገርሽ ሩቅ ነው መንገዱ ጉራጉር በቶሎ አይደረስ፤
እድሌ ተሳክቶ ምነው አንድጊዜ አይቼሽ ብመለስ።
ወይልብሽ አይራራ አንድ ቀን እንደሰው፤
ይብላኝልሽ ላንቺ ስፈልግሽ ኑሬ አንዴም ሳላገኝሽ እኔስ መሄዴ ነው።
B
የኔዋ ሽቅርቅር የኔዋ ፈልሳሳ፤
ብቅ ጥልቅ እያልሽ ጎበኘሽኝ እሳ።
ወይ በብዙ መጥተሽ ቤቴን አልሞላሽው ፤
ሄድ መጣ እያልሽ ልቤን አሳሳሽው፤
ጉልበቴን አድክመሽ ውስጤን አሳመምሽው።
C
የመኖሬ ሚስጥር ልዩ ስጦታዬ ፤
እጥፍ ድርብ ሁነሽ ነይልኝ ሽታዬ ፤
አንቺ ብቻ እኮነሽ የኔ መከታዬ።
በትንሽ ተፍተፍ በትንሽ ፉጨራ፤
ደከመብኝ ብለሽ ሆድሽ እየራራ።
የኔ ምስኪን አዛኝ ትመጫለሽ ቢሉኝ፤
አንድም ቀን ሳላስብ ሁልጊዜ ተኛሁኝ።
ጊዜም አትሻሚ እንቅልፍም አትነሺ ሁሉን አስከባሪ፤
እኔን እንዳይከፋኝ ሺህ ሁነሽ ነይና ደስታን አብስሪ።
የኔ ዲሞክራቲክ የኔ ሚዛናዊ ሁልጊዘም ነይልኝ፤
እኔስ መሄዴ ነው አንቺን እንዳይከፋሽ ዘላለም ኑሪልኝ።
D
ከተቀመጥኩበት ፈልገህ አታጣኝ ፤
ምናለ አንዳንዴ እንኳን ፊትህን ብትነሳኝ።
አንተ የኔ ጀግና የኔ ልበ-ሙሉ፤
ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ነህ አሉ።
F
የኔ አዶልፍ ሒትለር የኔ ሙሶሎኒ ምንኛ አስመረርከኝ፤
እኔ ምን አልኩና ሕይወቴን ለማጥፋት ቁማር ቆመርክብኝ።
ስራህ እንደ ሒትለር አንጀትህ አይራራ፤
ከመጣህ ላትሄድ ቢወድቁ ቢነሱ ቢያለቅሱ በተራ።
እንዳንተ አይነት ጨካኝ እንዳንተ አይነት ክፉ፤
ከየትም አይገኝ ቢለፉ ቢለፉ።
አንተም እኔን ሰደህ ደስታን ካገኘህ፤
ይብላኝ ለከራሚ እኔስ ሄድኩልህ።


ለማን ላድርስላችሁ ?
Merobi