Get Mystery Box with random crypto!

​​➛➛ተፈጥሮን ደጅ ልጥና➛➛ ' እኔ ልሙትልሽ' እያልኩኝ አልምልም ቃላቴን መንዝሬ፣ለሞት ቀብድ | ከደራሲያን አለም

​​➛➛ተፈጥሮን ደጅ ልጥና➛➛

" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፣ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፣ ታጠበ ሸሚዜ።

ገደብ ጫፍ በሌለው፣ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፣ ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፣ ከፎቅ ላይ አልወድቅም።

በሀኪሙ ስተት ፣በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፣ ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ፣ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፣ሽጉጤን አልጠጣም።

የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ ፣ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፣ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፣ ከመሞት ምን ሊገኝ?

➛ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም

Good night

#share

@ezuhmethiopia

@ezuhmethiopia

@ezuhmethiopia

@ezuhmethiopia

#share<

➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟➟