በሆነብህ ጥቃቅን ችግር የሆነልህን መልካም ነገር አትርሳ:: - ለፀሎት ጊዜ ብትጣም "ተመስገን!" ለማለት ጊዜ አታጣም! አፍህ በምስጋና ሲሞላ ህይወትህም በበረከት ይሞላል:: - “አዲስ ነገር ቢሰጠኝ እደሰታለሁ!” አትበል::አሁን በሰጠህ "አሮጌ!" ነገር ካልተደሰትክ ምንም ነገር ቢሰጥህ አትደሰትም:: - ምስጋና አምላክን ወደ አንተ የሚያቀርብ ማግኔት ነው::ልብህን ከአምላክህ ልብ የሚያገናኝ መድረክ ነው::ለራስህ ብለህ አምላክህን አሁን አመስግነው:: - በገጠመህ ጊዚያዊ መከራ ነፍስህ አማርራ ከአምላክህ ጋራ አትጣላ:: - ከተጣላህም ተመስገን ካልከው አይጠላህም:: - ተመስገን! #share @ezuhmethiopia @ezuhmethiopia @ezuhmethiopia @ezuhmethiopia #share