Get Mystery Box with random crypto!

የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የፊታችን ሰኞ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የፊታችን ሰኞ በኬኒያ ሊገኛኙ ነዉ

በደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

አምባሳደሩ ሬድዋን ሁሴን የስምምነት ሂደቱን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ ሲል አል አይን ዘግቧል።

በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የነበረው የድርድር ውጤት በሳለፍነው ረቡዕ ምሽት ይፋ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፤ በድርድሩ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች ውስጥም ግጭትን በዘላቂነት ማቆም፣ ሰብዓዊ እርዳታን ያለገደብ ማድረስ፣ በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ህግና ስርዓትን ማስከበር አንዲሁም የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታትየሚሉት ተጠቃሾች ናቸው።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያቸው ፤  በስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የፊታችን ሰኞ በኬንያ ናይሮቢ እንደሚገናኙ እና ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ውይይት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን እና በህወሓት በኩል ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ 10 ገፆችና 15 አንቀፆች ባሉት የሰላም ስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ የህወሓቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የተደረሰው ስምምነት ትልቅ ብስራት ነው ማለታቸዉ ይታወሳል።

የሰላም ስምምነቱን ቀዳሚ የሆነዉን ህወሓት ትጥቅ በሚፈታበት ዙሪያ ለመናገገር እና ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች የፊታችን ሰኞ በኬኒያ ሊገናኙ መሆኑ ተገልጿል።


@Ezmerejaet
@Ezmerejaet