Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር መረጃ በመንግስትና በህወሃት መካከል የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ሰበር መረጃ

በመንግስትና በህወሃት መካከል የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የህወሓቱ ተወካይ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በፊርማቸዉ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋንና አቶ ጌታቸዉ ረዳ ስምምነት ላይ የተደረሱባቸዉን ነጥቦች በጋራ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ተወካዮች  ፊርማቸዉን ካኖሩ በኋላ እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።

ቁልፍ የስምምነት አጀንዳዎች፦

- ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፤ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤
- ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ 24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር እንደሚያደርጉ፤

- ስምምነቱ በተፈረመ 5 ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
- የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
- ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
-በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል።
- በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
- የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል።
- መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል።
- ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
- የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
- ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል።
- እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet