Get Mystery Box with random crypto!

3 የአልሸባብ አባላት በሞት ተቀጡ። የጎረቤታችን ሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2018 | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

3 የአልሸባብ አባላት በሞት ተቀጡ።

የጎረቤታችን ሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2018-2020 መካከል ባለው ጊዜ የ15 ሰዎችን ህይወት በቀጠፉ ጥቃቶች ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ 3 የአልሸባብ አባላትን በሞት ቀጣ።

ሰዎቹ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው ሰኞ ማለዳ በሞቃዲሾ ውስጥ ነው ተብሏል።

ሶስቱ የአልሸባብ አባላት በ2019 የመንግስት ባለስልጣናት እና በርካታ ሲቪሎችን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ጥቃቶችን መፈፀማቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያ የሃይማኖት ሊቃውንት በይፋዊ መግለጫ ለ " አልሸባብ ገንዘብ መስጠት / መክፈል ሀራም ነው " ሲሉ አውጀዋል።

ቡድኑን ለመዋጋትም አንድነት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

በሃይማኖት ሊቃውንቱ እና በፌዴራል እና በክልል የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስቴር መካከል በተካሄደ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ መግለጫው የወጣው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet