Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከተደረገው ስምምነት ራሷን አገለለች | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ሩሲያ ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከተደረገው ስምምነት ራሷን አገለለች።

ሩሲያ ከዩክሬን ወደቦች የተከማቸ የምግብ እህል ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ በተመድና ቱርክ አሸማጋይነት ከዩክሬን ጋር ከደረስኩበት ስምምነት "ራሴን አግልያለሁ" ብላለች። ሩሲያ ቅዳሜ'ለት ውሳኔዋን ያሳወቀችው፣ "ዩክሬን ጥቁር ባሕር ላይ በነበሩ መርከቦቼ ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽማለች፤ ከዩክሬን ወደቦች እህል የሚጭኑ መርከቦችም የጥቃቱ ዒላማ ሆነዋል" በማለት ነው።

ተመድ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህበረትን ጨመሮ በርካታ ሀገራት የሩሲያን እንርምጃ የተቃወሙ ሲሆን፤ ሩሲያ በበኪሏ እርምጃው በዩክሬን ግዴለሽ ተግባር የመጣ ነው ብላለች። የሩሲያና ዩክሬንን ስምምነት ተከትሎ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያዊያን ተረጅዎች ከአንድም ሁለቴ በ10 ሺዎች የሚቆጠር ስንዴ ከዩክሬን ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዙ ይታወሳል። የሩሲያ ውሳኔ ዩክሬን ምርቶቿን ለውጭ ገበያ እንዳታቀርብ እንቅፋት ይሆናልም ተብሏል።

via - Alain

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet