Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ወጣት

የቴሌግራም ቻናል አርማ excellent_youth — መልካም ወጣት
የቴሌግራም ቻናል አርማ excellent_youth — መልካም ወጣት
የሰርጥ አድራሻ: @excellent_youth
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.49K
የሰርጥ መግለጫ

ዓላማችን ወጣቱን ትውልድ የተቀደሰ እና ለእግዚአብሔር የተለየ ማድረግ ነው።
በቻናሉ ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርቶች፤ አነቃቂ ጽሑፎች፤ ግጥሞችና የተመራረጡ መዝሙሮች ይገኛሉ። እኛ ለመስራት እንነሳ እንጂ ጌታ ሁሌም ይረዳናል!

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:40:56 መውደቅን አትፍራ

ቴክሳሶች እንዲህ ይላሉ፦ " ላሚቱ ትኑር እንጂ ወተቱ ቢደፋ አትጨነቅ"

ይህ ማለት ዛሬ ያለብከው ወተት ተደፋ ብለህ አቅጣጫህን አትሳት ገና ያልታለበ ወተት አለህ ማለት ነው። ላሚቱ እኮ ነገ ከ50 ሊትር በላይ ልትታለብ ትችላለች አንተ ግን ዛሬ በተደፋው አንድ ሊትር ወተት ጨጓራህን አትላጥ።

አንዳንድ ጊዜ በስኬት መሐል ውድቀት ያጋጥማል፤ በስራ መሀል ስህተት ይፈጠራል፤ በጠበከው መሐል ያልጠበከው ይከሰታል። ውድቀት ፍርሀትን ይፈጥራል። አዲስ ቢዝነስ ጀምሮ የከሰረ ሰው ሌላ ቢዝነስ ለመጀመር ይፈራል፤ የፍቅር ግንኙነት ጀምራ የተጎዳች ልጅ ከሌላ ሰው ጋር ለመጀመር ትፈራለች።

ውድቀትን አትፍሩ! ሙሴ ሰው በመግደል፣ ያዕቆብ አባቱን በማታለል የውድቀት ታሪክ ነው የጀመሩት።

ውድቀት በህልማችንና በፍፃሜያችን መካከል ያለ ገደል ነው። ቆርጠን ከተነሳን የምንሻገረው አለበለዚያ ግን ከፍፃሜያችን አርቆ በህልማችን ብቻ የሚያስቀረን አደገኛ ጠላታችን ነው።

የትኛውንም ዓይነት ስህተት ሰርተህ ውድቀት ውስጥ እንደገባህ ቢሰማህ ውድቀትህን ባስከተለብህ ለውጥ አትመዝነው። ትልቁ ውድቀት ውድቀትን ቋሚ አድርጎ መቀበል ነው።

ዛሬ ብትወድቅ ነገ የምትነሳበት ቀን ነው። የዛሬ ስህተትህ ጠባሳ አይደለም አንድ ቀን ይለቃል። ካንተ የሚጠበቀው ሁለተኛ ለመነሳትና ለማደግደግ እድል እንዳለህ ማወቅ ነው።  ጥረትህን ቀጥል

በአዶኒ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
1.4K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:40:53 ተግባራዊ እምነት ተአምር ይፈጥራል

እያንዳንዱ መጥፎ አጋጣሚ ከራሱ ጋር የተያያዘ እድል አለው፡፡ እንቅፋትን እንደ ውድቀት እስካልተቀበልነው ድረስ ውድቀታችን አይሆንም፡፡ ብዙ ሰዎች ተፈትነው የሚወድቁት ሽንፈት ባጋጠማቸው ጊዜ ራሳቸውን ምንም መስራት እንደማይችሉ አድርገው መቁጠር ሲጀምሩ ነው፡፡

በሽንፈታቸው ውስጥ አቻውን የአሸናፊነት ዘር ፈልጎ ከመጀመር ይልቅ፣ የበታችነት ስሜት በማዳበር ራሳቸውን ለድብርትና ለስሜት መለዋወጥ ይዳርጋሉ፡፡ ከዚያ ይልቅ ግን ሽንፈታቸውን እንደ አዲስ የመጀመሪያ መታጠፊያ ነጥብ መቁጠር ይገባቸዋል፡፡

ፈተናዎች የዕድል በሮች ናቸው፡፡ በምሳሌ እናስደግፈው፡፡ የሕይወቴ ትልቁ ፈተና እናቴን በዘጠኝ ዓመቴ ማጣቴ ሲሆን፣ በሚገርም ሁኔታ ያጋጠመኝም ትልቁ እድል እርሱ ነበር፡፡ ምክንያቱም እናቴን ተክታ የመጣችው የእንጀራ እናቴ ሕይወቴን ፈር ያስያዘችልኝ ታላቋ ቀማሪ ሆነች፡፡ እርሷ ባትኖር ኖሮ እንደ ዘመዶቼ ልጆች አልኮሌን እየተጋትሁ የምደባደብ ብኩን ልጅ ከመሆን የምድንበት ምክንያት አይኖረኝም ነበር፡፡

እያንዳንዱ ፈተና የዕድልን ዘር የያዘ ነው የምለውም ለዚህ ነው፡፡

ለአንድ አባት አዲስ የተወለደው ልጁ ምንም ዓይነት ጆሮ እንደሌለውና ዘመኑን ሙሉ መስማት የማይችል መሆኑን ከመስማት በላይ ምን አሳዛኝ ዜና አለ? በሚያስደንቅ መልኩ በእምነቴ የተነሳ ያ ዘመኑን ሙሉ ምንም መስማት አይችልም የተባለው ልጄ በቴክኖሎጂ እርዳታ መቶ በመቶ እንደማንኛውም ጤነኛ ልጅ መስማት የሚችል ለመሆን ቻለ፡፡ የእምነቴን ኃይል ተጨባጭ በሆነ ውጤት በተግባር አየሁት፡፡

ተግባራዊ እምነት ተአምር መፍጠር እንደሚችል የመጀመሪያ ምስክር እኔ ነኝ፡፡

ወደ ሀብት ጉዞ መጽሐፍ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
3.4K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:44:28 ራስን መሆን

ራስህን ስትሆን ሰዎች ላይወዱህ ይችላሉ፤ አስቂኝ ነገር...አይነግሩህም እንጂ በውስጣቸው እነሱም እንዳንተ መሆን ይፈልጋሉ። ወዳጄ በምንም አይነት ከባድ ሁኔታ ውስጥ ያመንክበትን ከማድረግና ራስህን ከመሆን ማቆም የለብህም!

ጓደኛ ምረጥ

ሁሉንም ነገር አስመስለን አንዘልቀውም። አንድ አይነት ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ፤ በዙሪያህ ካሉ ሰዎች መካከል ወደፊት እንዳትጓዝ የያዘህ ካለ እሱ ካንተ ጋር አብሮ ለመብረር አይገባውም ማለት ነው።

እህቴ ሴት ጓደኞችሽ ጋር ስትቀላቀይ መረጋጋትና ደስታ ካልተሰማሽ ለምን አብረሻቸው ትሆኛለሽ? በስሜትና በመንፈስ ካልተግባባችሁ አብራችሁ መዋላችሁ ለከንቱ ነው ማለት ነው፤ እሱማ በግም በግጦሽ ብዙ ወዳጆች አሉት ከመታረድ አያድኑትም እንጂ።

@Excellent_youth
@Excellent_youth
4.6K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:48:52 እልህ እልህና

የጥሉን ግድግዳ በስጋህ ያፈረስክ
ተጋርዶ የኖረውን መጋረጃ የቀደድክ
ህይወት የሆንክ አንተ የህይወት መግቢያ በር
ሙቱ ህያው ሆንኩኝ ስራህን ስቀበል

እልህ እልህና

የበዛ በደሌን በፍቅርህ የማርከው
ሀጥያት ሆነህልኝ ሀጥያት ያላወከው
አንተ በ'ኔ እንድትኖር ፈቅጄ ሙቻለሁ
መስቀሌን ልሸከም ራሴን ክጃለሁ

እልህ እልህና

ሰው በራሱ ስራ እንዳይፀድቅ አውቄ
በፀጋህ ድኛለሁ በፅድቅህ ፀድቄ
ወራሽ ሆኛለሁኝ ካንተ ጋር ባላገር
ላፍታ አይቀልብኝም የመዳኔ ነገር

እልህ እልህና

ወዳጅ ያደረከኝ ቀድመህ በመውደድህ
ልታከብረኝ ፈቅደህ እጅግ በመውረድህ
አጠናቀክልኝ ስራዬን ፈፀምከው
ህይወትን ልትሰጠኝ ቀድመህ ሞቴን ሞትከው

እልህ እልህና እልህ እልህና
እልህ እልሀለሁ መልሼ እንደገና
ኢየሱስ ማለቴን አልጠግበውምና

ሄኖክ አሸብር

@Excellent_youth
@Excellent_youth
5.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 20:52:30 ባዶ ሆኖ መሞት

ታርክ ሳያጠናቅቁ በሞቱ ታላላቅ ጅማሬዎች የተሞላ ነው። እንዲያውም በምድር ላይ ከሚኖሩት ከሰባት ቢልዮን በላይ ህዝቦች ውስጥ አብላጫው ሳያጠናቅቁ ይሞታሉ።

እንዴት ያሳዝናል! ቁም ነገሩ ያለው የጀመሪናቸው ነገሮች መጠን ላይ ሳይሆን ያጠናቀቅናቸው ላይ ነው። የውድድር አሸናፊ ፀንቶ የጨረሰ እንጂ ቸኩሎ የጀመረ አይደለም።

ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ አጠናቋል። በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት የተሰጠውን የቤት ስራ መወጣቱን፤ ተልዕኮውን በድል ማጠናቀቁን እንዲሁም ግዴታውን ማሟላቱን ያመለክታሉ። ጥልቅ የሆነ የሰላም ስሜት ያስተጋባሉ። እንዲሁም መሞቱን እንጂ አለመገደሉን ይናገራሉ።

<< ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ተፈፀመ አለ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን ሰጠ። >> ( ዮሐ 19፥30 )

እግዚአብሔር በውስጣችን ያስቀመጠውን ሁሉ ማለትም የተፈጠርበትን ዓላማ ፈጽመን ባዶ ሆነን እንዲንሞት ጌታ ይርዳን።

አናሲሞስ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
6.0K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 08:18:43 በአቋም መጽናት

በአቋም መጽናትን ምንም ነገር አይተካውም ተስጥኦ እንኳን አይተካውም። ተሰጥኦ እያላቸው ስኬታማ ያልሆኑ ሰዎችን እንደመመልከት የተለመደ ሌላ ነገር የለም። ጠቢብነትም ቢሆን በአቋም መጽናትን አይተካውም። ተግባራዊ መሆን ያልቻለ ጠቢብነት ከተረትነት አይዘልም።

ትምህርት ራሱ በአቋም መጽናትን አይተካውም። ዓለማችን በተማሩ ጎዳና ተዳዳሪዎች የተሞላች ሆናለች። ካልቢን ኮሌጅ

በአቋም መጽናት የጀመርነውን የመጨረስ ውሳኔ ነው። ተሸናፊ ሰዎች ስደክማቸው፤ ስያቆሙ #አሸናፊዎች ግን በጽናታቸው ይቀጥላሉ።

ስለዚህ ውጤታማ ለመሆን የምታደርጉት ጉዞ አልጋ በአልጋ አይደለም። ይልቁንም በመሰናክሎች የተሞላ አባጣ ጎርባጣ የሆነ ጉዞ በመሆኑ #በአቋም #መጽናት አለባችሁ።

@Excellent_youth
@Excellent_youth
6.5K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 20:34:23
የክርስቶስ ፍቅሩ

ሰማይ ምድር ሳይኖር ሳይፈጠር ሁሉ
ምንም ሳይገነባ ከአፍ ሳይወጣ ቃሉ
በሰማይ በምድር በባህር ውስጥ ያሉ
ሳይመጡ ወደምድር ሁኑ ሳይባሉ

ህያዋን ፍጥረታት በህይወት ሳይኖሩ
ወፎች ከየጎጆ መዝሙር ሳይዘምሩ
ወንዞች ከምንጫቸው ሳይፈልቁ ሳይወጡ
ሰዎችም መስዋዕት ለእርሱ ሳይሰጡ
ክብር ሳያመጡ

ማንም ሳያከብረው ክብር የተረፈው
ሞገስና ዝና የተትረፈረፈው
ሆኖ ሳለ ጻድቅ በዝቶ ሳለ ክብሩ
ወደምድር አመጣው አሸነፈው ፍቅሩ

በመካከል ኖረ በእጆቹ ስራ
የባሪያን መልክ ያዘ ቆመ በሰው ስፍራ
ከወንበዴ መሀል እርሱም ተካተተ
ስለሰው ልጅ ኖረ ስለሰው ልጅ ሞተ

ከፍ ሊያደርገን ወርዶ ሊያከብረን ተዋርዶ
ከውርደት ጀመረ በበረት ተወልዶ
እምባዬን ሊያብሰው ደሙን አፈሰሰ
ፍቅሩን ሊገልፅልኝ መከራን ቀመሰ
በክብሩ ሊያከብረኝ ውርደትን ለበሰ
በግርግም ጀምሮ በመስቀል ጨረሰ

ምናሴ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
5.6K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:16:11 ለቃሉ ታማኝ

(የሐዋርያት ሥራ 27: 25)

25፤ ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።

የሚታየዉና በሚታየዉ ዓለም ላይ ተገልጦ ያለዉ በሙሉ ከማይታየዉ ዓለም የመጣ ነዉ። በዚህም የሚታየዉ ዓለም የሚገዛዉ በማይታየዉ ዓለም ስልጣን ነዉ። ይህም ስልጣን ደግሞ ለእግዚአብሔር ልጆች የተሰጠ የልጅነት መብት ነዉ።

አንድ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ከእግዚአብሔር በመወለድ ያገኘዉን ስልጣን መግለጥና መጠቀም የሚችለዉ በእምነት ነዉ። የእምነት ምንጭ ደግሞ የክርስቶስ ቃል ነዉ።

ጳዉሎስ፣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ እንደዚሁ የሚያደርግ ታማኝ አምላክ ነዉና አይዞአችሁ ብሎ በመናገር በእግዚአብሔር ላይ ያለዉን እምነቱን የገለጠዉ፣ መልካም የሚባል ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ ሳይሆን ከባድና ለህይወት አስጊ በሚባል ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ ነዉ።

ምንም እንኳን በከባድ ሁኔታ ዉስጥ ቢሆንም፣ ከባዱን ሁኔታ የሚያሸንፍበትን የክርስቶስን ቃል ሰምቶ ነበርና እንደ ሁኔታዉ ሳይሆን እንደሰማዉ ቃል በመናገር፣ እንደተናገረዉ ቃል ኖረ።

እግዚአብሔር ለተናገረዉ ቃል ታማኝ አምላክ ነዉና እኛም ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ በመሆን እንደ ሁኔታዉ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመናገር፣ እንደ ተናገርነዉም ቃል እንኑር።

በቢንያም ተስፋዬ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
6.2K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 20:50:25
ማን ፈጣን እንደሆነ ለማውቅ አቦ ሸማኔውን ከአራት ፈጣን ውሾች ጋር እንዲወዳደር አደረጉት።

ነገር ግን ውድድሩ ተጀምሮ ውሾቹ መሮጥ ሲጀምሩ አቦ ሸማኔው በመሮጥ ፈንታ ቁጭ ብሎ ይመለከታቸው ጀመር። ሁሉም የውድድሩ ተመልካቾች የአቦ ሸማኔው አለመሮጥ እና ከቦታው አለመንቀሳቀስ አስገርሟቸው "ምን ተፈጠረ ?" ሲሉ ጠየቁ!

...አንዳንዴ ምርጥ መሆንህን ለማስመስከር ከሁሉም ጋር መወዳደር መሞከር ሞኝነት ነው። ስድብም ነው። ጠንካራ መሆንህን ለማሳየት ከደረጃህ መውረድ አያስፈልግህም። አቅምህን፤ ኃይልህንና ችሎታህን ለሚገባ ነገር ብቻ አውሉው።

@Excellent_youth
@Excellent_youth
6.4K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 21:27:50 እድላችሁን አታበላሹት

አእምሯችሁን ለመቆጣጠር ባለመቻላችሁ የምትከፍሉት ዋጋ ለክስተቶች ተገዢ መሆንን ነው፡፡ ሕይወታችሁ ባልተጠበቁ አጋጣሚዎች ስር ይወድቃል እንጂ መቼም በቁጥጥራችሁ ስር ሊሆን አይችልም፡፡ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ ልክ ነፋስ እንደሚያወዛውዘው ቅጠል ይሆኑባችኋል፡፡

ምድራዊ ዕጣ-ፋንታችሁን በራሳችሁ የምትወስኑበት ዕድል ተሰጥቷችኋል፡፡ ይህንኑ ዕድል ለማይጠቀሙ ደግሞ አቻ የሆነ ምድራዊ ቅጣት አለው፡፡ የምትፈልጉትን ነገር ለመውሰድ ሰዎች ምን ይሉኛል አትበሉ፡፡ ሰዎች በእናንተ ሕይወት ወሳኞች አይደሉም፡፡ ማንም ሌላ ሰው የምትፈልጉትንና የማትፈልጉትን እንዲወስንላችሁ አትፍቀዱ፡፡

በእርግጥ የበፊት ሕይወቴ እንደዚያ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ተቀይሯል፡፡ ማንም የምፈልገውን ነገር ሊነግረኝ አይችልም፡፡ እንዲነግረኝም አልፈቅድም፡፡ የፈጣሪዬ ፍላጎት በራሴ ጉዳይ የመጨረሻው ወሳኝ ሰው ራሴ እንድሆን ስለሆነ፣ ውሳኔዬን አሳልፌ ስሰጥ ፈጣሪዬን እየተሳደብኩ ነው፡፡

በዚህ ምድር ላይ ማንንም ሊጎዳ የሚችል ምርጫ አላካሄድም፡፡ በሌላ ሰው ላይ የማደርገው ሁሉ በእኔ ላይ እያደረኩት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ይህ የምንጊዜም ወርቃማ ሕግ ነው፡፡

ራሳችሁንም፣ ሰዎችንም መረዳት አለባችሁ፡፡ እናም በዙሪያችሁ ያሉ አስቸጋሪ ሰዎችን ለመቅረብ ራሳችሁን ማስተካከል ይኖርባችኋል፡፡ በሕይወት እስከቆያችሁ ድረስ ሁልጊዜም አስቸጋሪ ሰዎች ያጋጥሟችኋል፡፡ አስቸጋሪ ሰዎችን በአንዴ ልትቀይሯቸው ባትችሉም፤ አቀራረባችሁን ግን መቆጣጠር ትችላላችሁ፡፡

ወደ ሀብት ጉዞ መጽሐፍ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
4.3K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ