Get Mystery Box with random crypto!

ትኩረት ለ ትግራይ ተማሪዎች እኔ የ አዲግራት ዩንቨርስቲ ነባር የ 4ተኛ አመት ተማሪ ነኝ ። ያው | 🇪🇹ኢትዮ University

ትኩረት ለ ትግራይ ተማሪዎች

እኔ የ አዲግራት ዩንቨርስቲ ነባር የ 4ተኛ አመት ተማሪ ነኝ ። ያው እንደምታውቁት በ 11/06/2013 የተፈጠረው የ ጎደኞቻችን ሞት ጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ከቶናል ። በእዉነቱ አይገባቸውም ነበር ምን ያህል ፈተናን ተጋፍጠው ለመመረቅ እንደበቁ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ነው።

የሳይንስ እና ከፋተኛ ትምህርት ሚኒስትር ስለ ነባር የ አዲግራት እና አክሱም ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ በ አፋጣኝ አፅንኦት ሰቶ ሊመለከተው እና መፍትሔ ሊያስቀምጥለት ይገባል።

ሁሉም ዩንቨርስቲዎች ተመራቃ ተማሪዎቻቸውን በሰላም አስመርቀው ሸኝተው ነባር ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው ማስተማር ከጀመሩ ወራት አልፈዋል። ነገር ግን ትግራይ ዉስጥ ባለው ጦርነት እና የ ዩንቨርስቲዎች መውደም ምክንያት ነባር ተማሪዎችን ለመጥራት አልተቻለም። በመሆኑም ተማሪዎች ከትምህርት ከራቁ 1 አመት ሞልቶቸው በስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ የሳይንስ እና ከፋተኛ ትምህርት ሚኒስትር ተማሪዎች ያሉበትን ችግር በመረዳት በየክልሉ የመቀበል አቅም ባላቸው ዩንቨርስቲዎች ገብተን የምንማርበትን ወይም ደሞ በበቂ አጀብ ወደ መቀሌ የምንገባበትን ነገር እንዲያመቻች በትህትና እንጠይቃለን።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝