Get Mystery Box with random crypto!

ባንኩ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ግለሰቦች እንዲያመለክቱ አሳ | 🇪🇹ኢትዮ University

ባንኩ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ግለሰቦች እንዲያመለክቱ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ አግባብ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ሰዎች ባንክ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንዲያመለክቱ አሳሰበ፡፡

ባንኩ መጋቢት 6 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር አስታውሷል።

በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቤቲንግ ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ መጠቆማቸውንም ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም "ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳችሁ ያልሆነውን ገንዘብ ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ እናሳስባለን" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝