Get Mystery Box with random crypto!

ከ 128 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል የተባለዉ የመጀመሪያው የኒወክለር ህክምና ማዕከል ስራ | 🇪🇹ኢትዮ University

ከ 128 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል የተባለዉ የመጀመሪያው የኒወክለር ህክምና ማዕከል ስራዉን መጀመሩ ተነግሯል

በኢትዮጵያ በተለይ በግሉ የጤና ዘርፍ የመጀመሪያው እንደሆነ የተነገረለት የኒዉክለር ህክምና ማዕከል ስራዉን መጀመሩን ያስታወቀው ፓዮኔር ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ለአጠቃላይ ግንባታው ከ 128 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎበታል።

በ 72 ሚሊዮን ብር የኒዉክለር ህክምና መሳሪያ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ለሀገሪቱ የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን ህክምናውን ለማግኘት ይወጣ የነበረዉን ከ 100 ሺህዎች በላይ ገንዘብ ወጪ ማስቀረት መቻሉ ተሰምቷል።

በመንግሥት ደረጃ ከ 10 ዓመት በፊት የተጀመረ ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናውን የሚሰጥ ማዕከል አለመኖሩ ተገልጿል ።

የኒውክለር ህክምና እጅግ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር የሚያመነጭ ንጥረ ነገርን (ራዲዮፋርማሲዪቲካል) በመጠቀም ለታካሚዎች የምርመራና የህክምና አገልግሎት የሚሰጥበት የህክምና ዘርፍ ነዉ።

በሁሉም የህክምና ዘርፎች ተፈላጊ የሆነዉ የኒዉክለር ህክምና በተለይ በካንሰር ፣ በልብ እና በነርቭ ታካሚዎች ላይ እጅግ ጉልህ አስተዋጾ እንዳለው ይነገራል።(ካፒታል)

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝