Get Mystery Box with random crypto!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታካሚዎችን ማስተናገድ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ከ | 🇪🇹ኢትዮ University

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታካሚዎችን ማስተናገድ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ከምንጮች መስማቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

ሆስፒታሉ በበጀት ችግር ሳቢያ ከፍተኛ የመድኃኒት አቅርቦትና የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች እጥረት ገጥሞታል መባሉን ዘገባው አመልክቷል። ከውጭ የሚገዙ መድኃኒቶችን መግዛት የማይችሉ ታማሚዎች ለሕልፈት እየተዳረጉ እንደኾነም የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል ተብሏል።

ሆስፒታሉ የሚተዳደረው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሥር ሲኾን፣ የሆስፒታሉ አስተዳደርም ሆስፒታሉ በጤና ሚንስቴር ሥር እንዳሉ መደበኛ ሆስፒታሎች ኹሉን የሕክምና አገልግሎቶች መስጠት አይጠበቅበትም ማለቱ ተጠቅሷል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝