Get Mystery Box with random crypto!

' የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት ይጀመራል ' - የት | 🇪🇹ኢትዮ University

" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው አገልግሎቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል ብሏል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ተቋሙ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫ የጊዚ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝