Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር 'ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና ለአቻ ግመታ' የወጣ መመርያ ፀድቆ ሥራ ላይ መዋ | 🇪🇹ኢትዮ University

ትምህርት ሚኒስቴር "ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና ለአቻ ግመታ" የወጣ መመርያ ፀድቆ ሥራ ላይ መዋሉን አስታውቋል፡፡

ሥራ ላይ ከዋለ አንድ ሳምንት ያለፈው መመርያው፤ የኃይማኖት ነክ ተመራቂዎች የትምህርት ማስረጃ የምዘና አገልግሎት እንደማያገኙ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ የደረሰውን ሰነድ በመጥቀስ ዘግቧል፡፡

የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ መሟላት ያለባቸው፦

- የሚረጋገጠው ማስረጃ ትምህርት ማጠናቀቁን ለማረጋገጥ የተጠየቀበት ማመልከቻ፣
- አስፈላጊ መረጃዎች በባለሥልጣኑ የመረጃ ቋት ውስጥ አስቀድሞ ማስመዝገብ፣
- የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ ሰርተፊኬት ማቅረብ፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት መሟላት ያለባቸው፦

- የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት፣
- የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ መግለጫ ሰርተፊኬት፣
- የዲፕሎማ ትራንስክሪፕት፡፡

የድኅረ ምረቃ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ መሟላት ያለባቸው፦

- የሁለተኛ ዲግሪ የምስክር ወረቀት፣
- የመመረቂያ ጽሑፍ፣
- የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕትና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡

በባለሥልጣኑ ዕውቅና ከተዘጋ ተቋም የተዘዋወሩ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው ተቀባይነት እንደማያገኝ ሰነዱ ያብራራል፡፡

የምዘና አገልግሎት ምስክር ወረቀት የጠፋበት ግለሰብ ሁሉንም መሥፈርቶች በድጋሚ በማሟላት ምትክ የምዘና ምስክር ወረቀት እንደሚሰጠው መመርያው ይገልጻል፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1