➹ ዕድሌ_ነው ➹ ❦ ዕድሌ ነው... በሚስት ልወሰን እኔ ትዳር ሲያምረኝ ሳታገባ ምትቆይ አንድም ሴት አትገኝ ❦ ዕድሌ ነው... እኔ ዲግሪ ስይዝ ዲግሪ ዋጋ ያጣል ገንዘብ ያለው ሁሉ ዶክትሬት ያመጣል ❦ ዕድሌ ነው... እኔ መድረክ ስይዝ ይፈታል ጉባኤ፤ እኔ መጾም ሲያምረኝ ይሆናል ትንሣኤ ❦ ዕድሌ ነው... በቁርባን ለመኖር ንሰሐ ስገባ አቁራቢው ፖትልኮ ቤተመንግሥት ገባ ❦ ዕድሌ ነው... እኔ ኳስ ስገዛ ሜዳው ይታረሳል እኔ ቤት ሲኖረኝ ሰፈሬ ይፈርሳል ❦ ዕድሌ ነው... ለተሾመ ሁሉ እንዳልኖርሁ ስለፋ እኔ አለቃ ስሆን የሚታዘዝ ጠፋ ❦ ዕድሌ ነውና... ከዕለታት አንድ ቀን መንገሤ ባይቀርም እኔ ንጉስ ስሆን ሀገሪቱ አትኖርም፡፡ ❦ ❦ Im Natnael Join @Ethiosakzon 2.0K viewsNatty, 18:12