Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭) ነቢዩ ዳዊት አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አ | ኢትዮጲስ_ዘኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ሚዲያ Ethiopis zeortodox Media

‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭)
ነቢዩ ዳዊት አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አምላካችን በዕልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ›› በማለት እንደተናገረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በዐርባኛው ቀን ዐርጓል።
በዕርገቱም ዕለት ሐዋርያት በተሰበሰቡበት እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እነሆ፥ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንት እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡›› ከዚያም እስከ ቢታንያ አውራጃ መውጫ ድረስ ወሰዳቸውና ባረካቸው፡፡ እየራቃቸውም ሄደ፤ በደመናም ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝም ተቀመጠ፤ ሐዋርያቱም ሰገዱለት፤ እጅግም ደስ ብሏቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ዘወትር በምስጋና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ (ሉቃ ፳፬፥፵፱-፶፪፣ማር፲፮፥፲፱)
እንኳን አደረሳችሁ!