Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ የሚያደርጉት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች ስፖንሰር ተደርጓል | ቡናችን👆

የኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ የሚያደርጉት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች ስፖንሰር ተደርጓል!

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን በማውጣት ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ከነዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ሁነቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጋቸው 30 ጨዋታዎችን ለስፖንሰሮች መሸጥ ነው።

ስፖንሰር የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በማህበራዊ ድህረ-ገፆቻችን እና በሬድዮ ፕሮግራማችን ምርት እና አገልግሎታቸውን ከጨዋታው ቀደም ባሉ ቀናት በተከታታይ የምናስተዋውቅ ይሆናል።

ከዚህ መነሻነት ይህንን ጥሪ የተቀበሉት የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች በደብረ ታቦር በዓል ላይ "ሆያ ሆዬ" በመጨፈር በታሪክ የመጀመሪያውን የአንድ ቀን ጨዋታ ስፖንሰር ማድረግ ችለዋል።

1, ብሩክ እስጢፋኖስ (ሳሞራ)
2, ደሳለኝ አሸብር (ደሱ ከማንአንሼ)
3, አዳነ ሽጉጤ
4, በእምነት መለሰ (ባሚ ኮፊ)
5, ደረጄ ተስፋዬ (ደሬ አንድአርገው)
6, እዩኤል ቢረዳ
7, ዊሊያም ሳምሶን (ነብሳ)
8, ፍቃዱ አበበ ( የቡና ዘር ሃረግ)
9, ብሩክ አሸብር
10, ኤርሚያስ አዳሙ (ኤርሚ በግጥም በዜማ)
11, ምንተስኖት አበበ
12, ሮቤል ገለታ
13, ዩሃንስ ጫላ
14, ስንታየሁ ጥላሁን (ሲንግል)
15, ዮናስ ሃይሌ (ዮኒ ኮፊ)
16, ዳንኤል ዘገየ
17 ማቲዎስ ተክለማሪያም
18 ስንታየሁ አዳሙ
19 መርከዝ እንድሪስ
20, ልኡል ግርማይ
21, እሸቴ ግርማ

"እናንት የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች ለክለባችሁ ያላችሁን አለኝታነት አሳይታችኋል እና ምስጋና ይገባችኋል"
የቡናዊያን የዘር ሐረግ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc