Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ድጋ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ እና ድጋፍ ሰጪ መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ-ስረዓት አስመረቀ። በ3500 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ መሰረተ ልማት ወደ ከተማዋ የሚጓዙ መንገደኞችን ምቾት ከፍ የሚያደርግና የአካባቢውን የቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ መልኩ የሚያግዝ ነው። ውድ ክቡራን መንገደኞቻችን ወደየትኛውም የዓለም ጫፍ ጉዞዎን ማድረግ ሲያሻዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ትኬት ቢሮ በአካል በመሄድ አልያም የሞባይል መተግበሪያችንን ወይም ድረገጻችንን በመጠቀም ትኬትዎን ገዝተው የማይረሳ ጉዞ ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ