Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘የኢትዮጵያ ተቋማት የስኬት ሽልማት’ን ተቀዳጀ። ብሔራዊ አየር መንገዱ ሽ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘የኢትዮጵያ ተቋማት የስኬት ሽልማት’ን ተቀዳጀ። ብሔራዊ አየር መንገዱ ሽልማቱን ከክቡር የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ ተቀብሏል። አየር መንገዳችን በአህጉር አቀፍ ደረጃ ላሳየው አመርቂ እድገት በተለይም በኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ላበረከተው ዓለም-አቀፍ አስተዋጽኦ ሽልማቱ ተበርክቶለታል። ሽልማቱን አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተቀብለዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ሽልማቱ ‘የመላው የአየር መንገዱ ሰራተኛ የትጋት ውጤት' መሆኑን ተናግረዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ