Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ እና የልዑክ ቡድናቸው | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ እና የልዑክ ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ተገኝተው ጉብኝት አደረጉ።
ክቡር አምባሳደሩና ልዑካኖቻቸው ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ ማኔጅመንት አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ስለ አጠቃላይ የአየር መንገዳችን የስራ እንቅስቃሴ እና የዕድገት ጉዞ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ክቡር አምባሳደር ማሲንጋ ከልዑካኖቻቸው ጋር በመሆን በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ዘመናዊ የሆኑትን የተለያዩ የስራ ክፍሎቻችንን ጎብኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ