Get Mystery Box with random crypto!

የአንጋፋው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ታሪክ አብነት የሆነችው እና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ተገጣጥማ በ | Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የአንጋፋው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ታሪክ አብነት የሆነችው እና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ተገጣጥማ በሀገሪቱ ሰማይ ላይ ናኝታ የነበረችው “ፀሐይ” አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለሀገሯ እንደምትበቃ በመስማታችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል።
ይህች አውሮፕላን ሀገራችን ዛሬ ለደረሰችበት የአቪዬሽን ዕድገት ፈር ቀዳጅ ከመሆኗም በላይ ለአቪዬሽኑ መስክ ዕደገት በየዘመናቱ ያለንን ቀናኢነት ማሳያ ምልክትም ናት። ይህች ብርቅዬ ታሪካዊ አውሮፕላን ለሀገሯ እንድትበቃ መንግስትን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት አበርክቶ ለነበራቸው አካላት ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ