Get Mystery Box with random crypto!

#EthiopiaCheck Monitoring በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተቋረጠው የኢንተርኔት | Ethiopia Check

#EthiopiaCheck Monitoring በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት።

ከትናንት ጀምሮ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲጋሩ ተመልክተናል።

የኢንተርኔት አገልግሎቱ መስተጓጎሉ የተሰማው የፌዴራል መንግስት የክልሉን ልዩ ሀይል ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ መሆኑንም መረጃውን ያጋሩት ሰዎች ሲገልጹ አስተውለናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የባህርዳር፣ የጎንደር እና የቆቦ ከተማ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን ከትናት ጀምሮ የሞባይል ዳታ አገልግሎት መቋረጡን ነግረውናል። የባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት ግን አለመቋረጡን ከነዋሪዎች ሰምተናል።

በተጨማሪም የስልክና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶች አለመቋረጣቸውን አረጋግጠናል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ የክልል ልዩ ሀይሎችን አፍርሶ በተቀመጡ አማራጮች መልሶ የማደራጀት ሥራ በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሁንና ይህን የመንግስት እርምጃ የሚቃወሙ ድምፅች መሰማት የጀመሩ ሲሆን እንደ አብን ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ተቃውመውት መግለጫ አውጥተዋል።

@EthiopiaCheck