Get Mystery Box with random crypto!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ ይቀጥላል። | ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱ ይቀጥላል።

በወጣው መርሃ ግብር መሰረት የ11ኛ ሳምንቱ ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 2015 ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት ሲካሄድ ከ14ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች ከጥር 23 እስከ መጋቢት 03/2015 ዓ.ም ከሐሙስ እስከ እሁድ ባሉ ቀናት በ9 እና 12 ሰዓት ይካሄዳሉ።

ፕሮግራሙም በምስሉ ላይ አያይዘነዋል!