Get Mystery Box with random crypto!

#ወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ ተቋሙን በተመለከተ በቅርቡ ተሰርቶብኛል ያለውን “ሐሰተኛ” ዘገባ በማስተባበል | Ethiopia 24

#ወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ ተቋሙን በተመለከተ በቅርቡ ተሰርቶብኛል ያለውን “ሐሰተኛ” ዘገባ በማስተባበል ዘገባውን የሰራውን ተቋም በህግ ተጠያቂ ሊያደርግ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲውን በተመለከተ በተሰራጨው ዘገባ ዙሪያ
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲው የተሰራውን ዘገባ የሚያጣራ ኮሚቴ በማዋቀር ባደረገው ማጣራት ምንም ፍንጭ እንዳላገኘ እና መረጃው "ሐሰት" ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል፡፡

ዘገባው "ሚዛናዊ ያልሆነ እና እጅግ ያልተረጋገጠ ሐሰተኛ" መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር)
"ከአንድ ግለሰብ (ዋና ሬጅስትራሩ) በስተቀር ዲግሪ በማተም ሂደት ማንም ሰው ሚና የለውም" ብለዋል።

"ማንም ተማሪ ዲግሪ የሚሰጠው በትምህርት ክፍል እና በኮሌጅ ተረጋግጦ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ መሆኑን" አመልክተዋል።

"ዩኒቨርሲቲው ላልተማሩ ሰዎች ዲግሪ በገንዘብ ይሸጣል" በሚል በጋዜጣው የተሰራው ዘገባ የዩኒቨርሲቲውን መልካም ስም የሚያጠለሽ መሆኑን ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት።

"ዩኒቨርሲቲው የህግ አግባብን ተከትሎ በአዋጅ ቁጥር 1238/50 መሰረት ጋዜጣውን ተጠያቂ እንደሚያደርግ" ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው የህግ ክፍል ቡድን ዘገባውን ከሰራው ጋዜጣ ጋር መነጋገር መጀመሩን እና ለመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ማሳወቁውንም ጠቁመዋል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24