Get Mystery Box with random crypto!

#በወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ። | Ethiopia 24

#በወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ 30 ሺህ 255 ተማሪዎችን ለዩኒቨርሲቲው መድቧል።

በዩኒቨርሲቲው ሦሥቱም ካምፓሶች 30 ሺህ 255 ተማሪዎች በሁለት ዙር የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ ተገልጿል።

በዚህም በመጀመሪያ ዙር 18 ሺህ 512 እንዲሁም በሁለተኛ ዙር 11 ሺህ 743 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ብሔራዊ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24