Get Mystery Box with random crypto!

ያሜናዳብ #ክፍል_አምስት ብዙ ሰው እያየን ነው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንደ ምንም | የፍቅር ደብዳቤ

ያሜናዳብ


#ክፍል_አምስት

ብዙ ሰው እያየን ነው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንደ ምንም ራሴን አረጋጋሁ በተለይ ጆን ወንበር ስቦ ልክ እንደ ፍቅረኛው ሲያስቀምጠኝ የሆነ
ነገር ውስጤ ላይ ተሰማኝ የሚገርመው…
እና በጣም ያሸማቀቀኝ ነገር ቢኖር ፍቅረኛዋ ጋርቁጭ ብላ ስጠቅሰው አይን በአይን አየኋት ከምንም በላይ ያናደደኝ መጥቀሷ ሳይሆን ፍቅረኛዋ ጋር ቁጭ ብላ ይሄን ማሰቧ ትንሽ ውስጤ ላይ ንዴት ነገር ፈጠረብኝ ትዙ ምነው ችግር አለ አለኝ እረ የለም አልኩ ፈገግ ብዬ ፊትሽ ላይ ጥሩ ስሜት አይታይም ሲል እሷ
ናት አልኩ አንገቴን እንደ መድፋት ብዬ ሳቄን መጦኝ እእእ ምንም ማድረግ አይቻልም መቻል ነው አለ እየሳቀ አልበላም ያልኩትንስ አንድ በአንድ በላሁ በዛ ላይ ጫዋታው በትንታ ገሎኝ ነበረ ልክ እንደኛ የተቀመጡ ሁሉ ሰረቅ እያደረጉ ያዩናል እኔም በልቤ ይታደሉታል
እንጂ እይታገሉትም እያልኩ ጫወታችንን ቀጠልን የጠጣሁት መጠጥ ግን በጣም ራሴን ያዘኝ ለካስ ስልፈው የነበረው ቮድካ ነው እኔ በስም እንጂ ቮድካን የት አውቄው እንደ ምንም ብዬ ልነሳ ስል ራሴን ሊያዞረኝ ፈለገ ቀስ ብዬ ራሴን አረጋግቼ ተነሳሁ ክፍል እንደ ደረስኩ አልጋው ላይ ተዘረርኩ ጆን በሁኔታዬ ይስቃል መጠጥ ነገር አትሞክሪም
እንዴ ብዙም እኮ አልጠጣሽም በትንሹ ደፍቶሽ ነበር አለ እየሳቀ እረ ተውኝ ባክህ ይሄንንም እኔ ሁኜ ነው አልኩ ብርድ ልብስ ውስጥ ገብተሽ ተኚ ብሎ ወጣ ወዴት እንደ ሄደ አላውቅም በቃ አልጋው ላይ ራሴን እንኳ ማንሳት አቃተኝ ቆይቶ ሲመጣ እንደ ነበርኩ አገኘኝ በጉልበቱ አልጋው ላይ እንደ መደገፍ አለና ወገቤን እና ጭኔ ይዞ ወደ ላይ አስጠጋኝ በህይወቴ ለመጀምርያ ግዜ ነው ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲይዘኝ በቃ ውሀ ሆንኩ ወደ ላይ አስጠጋኝና ጫማዬን አውልቆልኝ
።አስተኛኝ ድንጋጤም አለ ደስታም አለ ብቻ ካስተኛኝ በኋላ ንቅንቅ አላልኩም እሱ ከራሱ አልጋ ላይ ተኛ ጥዋት ስነሳ በጣም ራሴን አመመኝ ጆንን አልጋው ላይ ሳየው የለም ሻወር ቤት ውስጥ እየታጠበ ይሆናል አልኩ ድምፅ ስሰማ ግዜ
ትንሽ ቆይቶ ከሻወር ቤት ሲወጣ ደረቱን ሳይ ልቤ ድንግጥ አለ አንደ ግጥም ትዝ አለኝ ደረትህ ሰፊ ነው እንደ ንጉስ አልጋ ጎንህ ተሸጉጬ ዘላለም አይንጋ እያልኩ እንዳላዜምልህ እንዳልቀኝልህ በልቤ ነው እንጂ መቼ የኔ ሆንክና አለች በለግጥሟ
የእውነት በቃ ተመኘሁት ኧረ አይንሽ ንቀይ አለኝ አፍሬ አንገቴን ደፋሁ ሳቀብኝ ተነሺ ሻወር ግቢና ቶሎ እናግኛት አለኝ እኔም ጨራርሼ እንደ ወጣሁ ክላስ ድረስ ቁርስ መጣልን ሴትን ልጅ በፍቅር ነው ሚንከባከብ ምን ማድረግ አይቻልም ያልክ አንተ ነህ እያልኩ በልቤ እኔም ሚያደርግልኝን ሁሉ መቀበል ጀመርኩ ልክ ረፋዱ ላይ ፌቨንን አገኘናት አምሮባታል ሰላም ስትለኝ ጠጋ ብዬ በጆሮዋ ኧረ ሚስ ሀዋሳ ሆንሽብኝ አልኳት በጣም ሳቀች መጨረሻ ላይ ጆን ያለውን ነገር ነገራት ፊቷ ተለዋወጠ እኔ ወሬያቸው ምንም አልገባ አለኝ ያን ታክል አመት በቤተሰብ ፍቅር ሲሰቃይ የት ነበራቹ
አለች ፊቷን አጥቁራ ሁሌም ቢሆን ወንድሜ ራሱን ጥፋተኛ ማድረግ አይወድም አላት በቃ ብዙ ተጨቃጨቁ
ዛሬም ድረስ እንደዚህ ትወደዋለች እንዴ አልኩ በልቤ እሺ እውነቱን ልንገርሽ እናቱ ለእኔ እንጀራ እናት ናት ሲል ደነገጠች ታድያ እሱ እስከ ዛሬ ድረስ እኮ የአባቴን ልጅ በደልኩት እያለ እኮ ነው ራሱን የሚወቅስ አለች ጆን አንገቱን ደፋ ቆይ ቆይ አንተ ዘንድ አባትህ የሰጠህ ደብበዳቤ አለ እንዴ አለችው ጆን
በድንጋጤ አዋ አላት ከግዜ በኋላ አንድ ሊያደርገን የሚችል ቢኖር ያደብዳቤ
ነው ብሎ ነግሮኛል አለች ጆን ተነስቶ ሁለት እጆቿን ሳመው ደነገጠች እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ.....

ይቀጥላል
ከ 25 like በኋላ ይቀጥላል