Get Mystery Box with random crypto!

#የሰላምታ_አሰጣጥ #ክፍል_5 ሐዲሥ 132 / 856 አቡ ጁረይ አል ሁጀይሚይ እንዲህ ሲሉ አ | Muslim ሙስሊም

#የሰላምታ_አሰጣጥ

#ክፍል_5

ሐዲሥ 132 / 856

አቡ ጁረይ አል ሁጀይሚይ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ “ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ መጣሁና፦ “ዐለይከስ_ሰላም ያ ረሱሉሏህ (የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰላም ባንተ ላይ ይስፈን)” አልኳቸው። “ዐለይከስ_ሰላም አትበል፤ ዐለይከስ_ሰላም የሚለው አባባል የሙታን ሰላምታ ነውና” አሉኝ። (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የአላህ መልዕክተኛ የሰላምታ ዓይነትም አስተምረውናል።
2/ ትክክለኛው ሰላምታን “አስሰላሙ ዐለይኩም” የሚለው ቃል ነው። ሱንናውም እርሱ ነው። ይህን ቃል ሌላ አባባል ሊተካው አይችልም። ከአሁን ቀደም እንደተገለጸው “ደህና አደርክ”፤ ወዘተ. የሚለው አባባል ቀርቶ “ዐለይከስ_ሰላም” በማለት የቃላቱን ቦታ ማቀያየርን እንኳ መልዕክተኛው አልወደዱትም።

ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1