Get Mystery Box with random crypto!

#የሰላምታ_አሰጣጥ #ክፍል_4 ሐዲሥ 132 / 855 አስማእ ቢንት የዚድ እንዳስተላለፉት | Muslim ሙስሊም

#የሰላምታ_አሰጣጥ

#ክፍል_4

ሐዲሥ 132 / 855

አስማእ ቢንት የዚድ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ መስጊድ ውስጥ ሴቶች ተሰብስበው ተቀምጠው እያለ በአጠገባቸው አለፉ። በእጃቸውም የሰላምታ ምልክት አሳዩ። (ቲርሚዚ)
ይህ ሐዲሥ አቡ ዳውድ፦ “ሰላምታ አቀረቡልን” የሚል ቃል አክለው ካቀረቡት ዘገባ ጋር ሲጣመር ነቢዩ ለሴቶቹ የእጅ ምልክት ያሳዩት ከቃል ሰላምታ በተጨማሪ መሆኑን ያመለክታል።

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ በቃል ሰላምታ ማቅረብ የማይሰማ ከሆነ በምልክት ሰላምታ ማለት ይፈቀዳል። ቃል የሚሰማ ከሆነ ግን በምልክት ሰላም ማለት የተጠላ ነው። ምክንያቱም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ባሕል ነውና። ይህም በሌላ ዘገባ ተገልጿል።
2/ የአላህ መልዕክተኛ ለሴቶች ሰላምታ ማቅረባቸው ተመልክቷል። ለተቃራኒ ፆታ ሰላምታ ማቅረብ ፈተና ላይ ያለመውደቅ እና በመጥፎ ሐሳብ ያለመወስወስ እምነት ካለ ይፈቀዳል።
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1