Get Mystery Box with random crypto!

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ ሰኔ አካባቢ ፈተናቸውን እንዲወስዱ | Ethio Jobs Vacancy™

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ ሰኔ አካባቢ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ት/ት ሚኒስቴር አስታወቀ!

በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

#የተለያዩ መረጃዎች በቀላሉ በስልክዎ እንዲደርስዎ ይህንን ሊንክ ይጫኑት . https://t.me/joinchat/AAAAAFKyxw00jgDT-fxHaQ