Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ። _____________________ | Ethio Jobs Vacancy™

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ።
__________________________-

ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮሮና ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት የ2012ዓ.ምሀገር አቀፍ ፈተና ፈተናው የካቲት 29, 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ለተፈታኞች የፈተና መግቢያ መታወቂያም በየትምህርት ቤቱ ከ የካቲት 22 እስከ 24 ድረስ እንደሚሰጥ በመግለጫው ተነግሯል።

ከየካቲት 21-27,2013ዓ.ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በየቀኑ ለመከታተል ይህንን ሊንክ ይጫኑት . https://t.me/joinchat/AAAAAFKyxw00jgDT-fxHaQ