Get Mystery Box with random crypto!

ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን አሥራተ ካሣ እንዳተቱት አባቶቻችን የሠራሯት፣ ያበጃጇት፣ የኖሩባትና ታሪካቸ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን አሥራተ ካሣ እንዳተቱት አባቶቻችን የሠራሯት፣ ያበጃጇት፣ የኖሩባትና ታሪካቸውን የጻፉባት የታላቋ ሀገር የኢትዮጵያ ጥንታዊ ማንነትና ምንነት በዚህ ጥልቅ የታሪክ ፍሰት ማሳያ መጽሐፍ ግልጽ ሆኖ ቀርቦልናል። የታሪክ ተመራማሪና ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው በተባ ብዕሩ ተሰውሮብን የነበረውን ኢትዮጵያ ለዘመናት ያለፈችበትን ያልተገለጠ እውነት መጋረጃውን ገፎ፣ አቧራዋራውን አራግፎ “የታላቋ ኢትዮጵያ ዝክረ ታሪክ” በሚል ታላቅ ርእስ እንደ ስሙ ታላቅ የሆነ መጽሐፍ እነሆ ለንባብ አብቅቶልናል።
መጽሐፉ በዘመናት ሂደት፣ በሕዝቦች ዑደት የኢትዮጵያ በሮች ሲጠቡና ሲሰፉ፣ ሲላሉና ሲጠብቁ መዛግብቶቿን እየከፋፈተ ያሳያል፤ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ድርሳናት እያመሳከረ፤ በየዘመናቱ የሆነውን የዓለመ ሰብእን ክዋኔ እየመረመረ እነሆ ማንነታችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ ይለናል። የሀገራችንን የታላቅነቷን ምሥጢሮችም አንድ በአንድ እየዘረዘረ ወደ ቀደመው ታላቅነታችን ይጠራናል። ሃገራችን በሐሰት የትርክት ታሪክ እየተናጠች በምትገኝበትና ትክክለኛው ታሪካዊ እውነታ እየደበዘዘ ባለበት በዚህ ወቅት ነባራዊውን ሃቅ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ መዛግብትን በመመርመር በማስረጃ አስደግፎ የኢትዮጵያን ጥንታዊና የመካከለኛው ዘመን ታሪክ እንዲህ ገሃድ አውጥቶ የሚያስረዳና ለተመራማሪዎችም ትልቅ ዋቢ በመሆን የሚያገለግል ይህን የመሰለ ድርጁ የምርምር መጽሐፍ ማግኘት ትልቅ ገጸ በረከት ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው።
ዋና አከፋፋይ፦ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ቁ.1 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ.
ቁ.2 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ስ.ቁ.2519 11 00 67 05