Get Mystery Box with random crypto!

ማኪ ቡና 'ፋኖ እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፣ እንደ ነብር ቁጡ፣ እንደ እርግብ የዋህ ነው። በዚህ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

ማኪ ቡና "ፋኖ እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፣ እንደ ነብር ቁጡ፣ እንደ እርግብ የዋህ ነው። በዚህ ባሕርዩም አልጋ ላይ የዋለን በሽተኛ ጠያቂ፣ የተጣላውን አስታራቂ፣ የደከመውን አነቃቂ፣ ለእኔ ሳይሆን ለእኛ የሚል ክንደ ብርቱ የዓላማ ሰው ነው። ፋኖ ቁሞ ከሚሸነፍ ሞቶ ማሸነፍን የሥነ ልቡናው መሠረት ያደረገ የአሸናፊነት ምልክት ነው። ፋኖ የዐማራ ሕዝብ ሥሪት ሕያው ምስክር፣ በራሳቸው የሚተማመኑ ሀገር እና ወገን ወዳድ ስመጥር ጀግና ኢትዮጵያዊያን የክብር ስም ጭምር ነው። ፋኖነት በሕይወት እና በሞት መካከል በሚደረግ ብርቱ ትግል የሚገኝ ወርቃማ ስም ነው። ፋኖነት የዕድሜ፣ የፆታ፣ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሙያ፣ የዘር እና መሰል ልዩነቶችን ሳይፈጥርና ሳያጎል ሁሉም በተግባር ተመዝኖ በሚገለጥ እውነታ የሚገኝ እና ራሳቸውን ለሰፊው ሕዝብ ሲሉ አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች ክብር ስም ነው።"

ጌትነት ይርሳው ድንቅ መጽሐፍ ነው ያበረከትልን። በፋኖነት ዙሪያ ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖረን ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ሲመረቅ በቦታው ለመገኘት አስቤ ሳይሳካልኝ ቀርቶ ነበር። የዛውን ቀን አንዱ ወዳጄ ይሄን መጽሐፍ አንብቢው ብሎ በስጦታ አበረከተልኝ። እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ሌሎችም አንብቡት፣ በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚመርቁበት ወቅት ስለሆነ እንዲህ ያለ ስጦታ እየገዛችሁ አበርክቱላቸው።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ ፦
ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 0911006705

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02rcUHhjzFyTFhHfSCe4b3FmqbfX8A1S3Jsqwg6DB7zV83RaEWT1gNRQHtGH85e1DMl&id=101217292147212