Get Mystery Box with random crypto!

በወሳኝ ወቅት የተጻፈ ድንቅ መጽሐፍ። “ፋኖ ማለት እኔ ነኝ” በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት የቀድ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

በወሳኝ ወቅት የተጻፈ ድንቅ መጽሐፍ።
“ፋኖ ማለት እኔ ነኝ” በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት የቀድሞው የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳው “ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል።

በ6 ክፍሎች፣ በ26 ምዕራፎች እና በ428 ገጾች የተዋቀረው እና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ይኸ መጽሐፍ መታሰቢያነቱን “ትናንትን በፋኖነት ኑረውት ላለፉ፣ ለዛሬ ፋኖዎችና ነገን በፋኖነት ለሚኖሩ” ሆኗል፡፡ መጽሐፉ የፋኖነትን ህይወት ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን በፋኖነት እሴት ላይ አተኩሮ የተጻፈ ቀዳሚ መጽሐፍ እንደሆነ በመጽሐፉ አርትኦት ላይ ከተሳተፉ ታላላቅ ምሁራን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንጋፋው እና ከፍ ያለ የሞራል ልዕልና ያላቸው ሀቀኛው የፍልስፍና እና አንትሮፖሎጅ ምሁሩ ፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ በሰጡት አስተያየት “ሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ከዘር ልዩነት አልፎ፣ ከጎሳ ቅያድ ተርፎ፣ ከክልል ቅፍንድ ገዝፎ ሊያነበው የተገባ ልጨኛ መጽሐፍ ነው" ያሉ ሲሆን የመጽሐፉ ደራሲ የሆኑት አቶ ጌትነት ይርሳውን አስመልክቶ ደግሞ፤

“የሚያውቀውን እውነት የሚናገር፣ የሚናገረውን የሚሰራ እና የሚሰራውን የሚያውቅ ብእረኛ መሆኑን ያሳየበት ብሉይ መጽሐፍ ነው ÷ ፋኖነት፡፡” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፤

መጽሐፉ በቅርቡ የተለያዩ እንግዶችና ደራሲያን በተገኙበት እንደሚመረቅ ታውቋል፡

የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ፣ ሀሁ መጻሕፍት መደብር ሲሆን፣ አድራሻው፦
ቁ.1. አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2. ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 09 11 00 67 05