Get Mystery Box with random crypto!

ቅን መሪዎችን መታደል ለአንድ አገር ትልቅ ሀብት ነው። አገር በመሪ ይነሳል ፤ በመሪም ይወድቃል። | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

ቅን መሪዎችን መታደል ለአንድ አገር ትልቅ ሀብት ነው። አገር በመሪ ይነሳል ፤ በመሪም ይወድቃል። በመሪ ብልጽግና ይገኛል ፣ መሪ ሊያራቁትም ይችላል። በመሪ ፍትሕ ይሰፍናል፣በመሪ ፍትሕ ይጓደላል። በመሪ ስነ ምግባር ይስፍፍል፣በመሪ የሞራል ዝቅጠት ይመጣል። በመሪም እምነት ይጸናል ፣ በመሪ እምነትም ይጠፍል። መሪ ይከፋፍላል፣ መሪ የተበታተነውን ያሰባስባል። መሪ የግጭት ምንጭ ይሆናል፤ የጠፋ ሰላምም በመሪ ይመለሳል። በመሪ አገር ይሰፋል፣ በመሪም አገር ይጠባል።

ችግራችን ከሌሎች አገሮች የተለየ አይደለም። ችግራችንን የተለየ የሚያደርገው አገልጋይነት በበቂ ሁኔታ አለመለመዱ ነው። ችግራችንን ለየት የሚያደርገው ቅን መሪዎችን ማጣታችን ነው።

በቀና አስተሳሰብ ፣በቀና አመለካከት ትልቅ ሕልም ያለው ብቻ ሳይሆን ትልቁን ሕልሙን በቅንነት ለመፈጸም የሚተጋ ፣ በሚሰራው ሁሉ በታማኝነት የሚመሰክርለት ፣ ለእውነት የቆመ ፣ አድሎን የሚጸየፍ፣ ለፍትሕ የሚያደላ መሪ። ችግር የሆነው የነበረንን ፈሪሃ እግዚአብሔር እና ግብረ ገብነት ስናቃልለውና ግብረ ገብ መሪዎችን ስናጣ ነው።
ከእኛ አገራችን ትቅደም ፤ እኛ ተጎድተን አገር ትበልጽግ ፤ እኛ አልፈን አገር በነጻነት በሰላም ትኑር የሚሉ መሪዎች የበዙባቸው አገሮች ከወደቁበት ሲነሱ፣ የጎበጠው ወገባቸው ሲቃና ለማየት የተቻለበት ዘመን ላይ ነው ያለነው።
ይህ ሁሉ የሚገኘው ለሥልጣን ያለው እይታ ሲስተካከል ነው። በጎቹን የሚነዳ ሳይሆን የሚመራ ፣ ምንደኛ ሳይሆን መልካም እረኛ ሲገኝ አገር ትበለጽጋለች።
ቅን መሪ

ሀሁ መጽሐፍት መደብር

አድራሻ ቁ. 1 ስታድየም ናሽናል ታወር ግራውንድ ፍሎር
2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ

ስ.ቁ 0911006705