Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶ | ስብዕናችን #Humanity

ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል

የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶሎ ለመድረስ ብለህ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም። ልብህ በእውነት ላይ ተረማምደው በሰዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ፣ በአቋራጭ ባደጉ ሰዎች እንዳይቀና! የግፍንም እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ ፣ትግስትን ገንዘብህ አድርጋት አምላክ ለአንተ ያዘጋጀዉ ነገር አለውና። በዕውነት ፣ በሃቅና በራስ አገዝ አዋጭ መንገድ ከተራማድክ እመነኝ በያንዳንዱ እርምጃህ ስኬትህን እየገነባህ ነው።

ሀሴትህ በቀናነትህ መጨምር ይበዛል፣ ከክፋት ትርፍ አይሰበሰብም፡፡ የምትሆነው ብታጣ እንኳ ጨካኝነትን ብቸኛው ምርጫህ አታድርግ፡፡ የሚመረጥ ስላጣህም የማይመረጥ አትምረጥ ፣ የምትመርጠው ከሌለ አለመምረጥም ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ማስተዋልህን ባለማስተዋል አትጠቀምበት፡፡

ወዳጄ ሆይ

ከብረህ ሳለም ቀለህ መኖርን አትውደድ፡፡ በከፍታ እንጂ በዝቅታ እያሰቡ መኖር አይመጥንህም ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል፡፡ የውስጥህንም ሰላም ያመክናል፡፡ጊዜአዊ እንጂ ዘላለማዊ የዚህች ምድር ነዋሪ አይደለህምና በደጉ ጊዜህ መሰልህን አትበድል፡፡

ነገ የአንተ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በውል አታውቅምና ነግ በእኔ ማለትን እወቅ፡፡ በቁንጮነት ዘመንህ የፍጡራንን መብት አትግፈፍ፡፡ የሌላው ውድቀት የአንተን መቆም አያረጋግጥምና ፣ መከራ በታጨቀባት በዚህች ጠፊ ዓለም መልካምነትን የመሰለ ሰላም ሰጪ ተግባር የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬህ ላይ ነገ የማትፀፀትበትን ምግባር አብዛ፡፡

ነፃ የሆነ ነፃነት እንዲሰማህ ፤ በጭንቀት የታጨቀ ኑሮህን በቅንነት ቀይር፡፡ ከሁካታ እርካታ አይመነጭም እፎይታ ለሚሰጡህ ተግባሮች ራስህን ስጥ፡፡
ሐዋዝ

ውብ ምሽት

@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot