Get Mystery Box with random crypto!

ፍርሀት  በአእምሮአችሁ ውስጥ ሊኖር የሚችል ሀሳብ ነው።ይህን ሃሳብ በጠንካራ እምነት፣በስኬትና በድ | ስብዕናችን #Humanity

ፍርሀት  በአእምሮአችሁ ውስጥ ሊኖር የሚችል ሀሳብ ነው።ይህን ሃሳብ በጠንካራ እምነት፣በስኬትና በድል አድራጊነት ሃሳቦች በመተካት ከስሩ ፈንቅላቹ ልታወጡት ትችላላችሁ።ሁል ግዜም  በራሳችን ላይ እምነትን ካሳደርን፣የማናሸንፍበትና ደስተኞች የማንሆንበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።ደስታህን በራስህ ፈልገው።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው .ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚሉት። የመረጋጋት ችሎታ በጣም አስፈላጊ እና ብዙ ጊዜ ሰዎች ጋር የማይታዩ የህይወት ችሎታዎች አንዱ ነው። በጣም መጥፎውን ውሳኔ የምንወስነው ሰላማችንን አጥተን ወይም ስንጨነቅ እና ግራ ስንገባ ነው።

ፍርሃት እውነተኛና መሰረታዊ ችግሮችን የመፍታት አቅማችንን በእጅጉ ሊያጠፋው ይችላል። ተረጋጋክ ማለት ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እና በደስታ ያበቃል ማለት አይደለም።ነገር ግን በተሻለ የአዕምሮ ሁኔታ የህይወታችንን እውነተኛ ፈተናዎች እንጋፈጣለን ማለት ነው።

ታዋቂው ፈላስፋ አለን ዋትስ ፍርሀትን ስለማሸነፍ  ያተናገረውን ድንቅ ንግግር ከስር ባለው ቪዲዮ ተጋበዙልን

           ውብ አሁን