Get Mystery Box with random crypto!

ምክር  ለወዳጅ ወዳጄ ሆይ! ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ | ስብዕናችን #Humanity

ምክር  ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ!

ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም።ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ።

ወዳጄ ሆይ!!

አግኝቶ ያጣው ቶሎ ይከፋዋልና ታገሠው ። አጥቶ ያገኘ ምድር ይጠበዋልና ምክረው ። ከፍታህ ዝቅተኞችን በመርገጥ ፣ ህልውናህ በሌሎች ሬሳ ላይ አይሁን ። የፍቅር ሰው ለመባል ሁሉም ትክክል ነው አትበል ። ግልጽ ጥላቻ የፍቅር ያህል ነው ። ግልጽ ንግግር ሰሚውን ያከበረ ነው ። እጅግ ግልጽነትም የሚያስገምት ነው፣ ።የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ። ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ።


ወዳጄ ሆይ!

ለዕውቀት ትጋ ፣ በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስክን እንደ አዋቂ አትቁጠር ። በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል ። "ሥራ ስትሠራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው" ፣ በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ። እርኩሰት የዕውቀት እና ስልጣን መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ ። "

እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ። ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናወን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ።

             ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot