Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም የታነፀችው ከሐሳብ ነው፣ ሐሳብ የሁሉ ነገር አልፋ ነው። ሁሉም ሐሳቦች ግን መልካም ናቸው ማ | ስብዕናችን #Humanity

ዓለም የታነፀችው ከሐሳብ ነው፣ ሐሳብ የሁሉ ነገር አልፋ ነው። ሁሉም ሐሳቦች ግን መልካም ናቸው ማለት አይደለም፣ መልካሞቹ ግን በህሊና ቅኝት የተቃኙት ናቸው!

ጥበብ ማስተዋል ነች! ማስተዋል ደግሞ ከዕርጋታ/ከስክነት ትወለዳለች!ሁሉም ሰው በሌላ ሰው አይን ስህተት ሊሆን ይችላል። በራሱ አይን ግን ሁሉም ሰው ትክክል ነው!

በውይይት መግባባትም/አለመግባባትም ተፈጥሯዊ ነው። መሠረታዊው ቁምነገር የሐሳብ ብዝሃነትን ማስተናገድ መቻል ነው።የሠላ አዕምሮ በምክንያታዊነት ተነጋግሮ መደማመጥን ይከጅላል።አንድን ነገር ስለተቃወምነው ስህተት ነው ማለት አይደለም። ስለደገፍነውም ደግሞ ትክክል ነው ማለት አንችልም!በስሜት ከደገፍነው ይልቅ በሐሳብ የሞገትነው በብዙ ሺ እጥፍ ፍሬ ያፈራል!

ምግብን ማላመጥ እንደምናውቅ ሁሉ ሐሳብን ማላመጥ እና ማብላላት መለማመድ ይኖርብናል። የሰጡትን የሚቀበለው ሆድ ብቻ ነው። አዕምሮ ደግሞ የሆድ ባህሪ የለውም። ነገር ግን እንዲሆን ከመረጣችሁ መሆን አያዳግተውም፤ ምክንያቱም አዕምሮ የልምምድ ባርያ ነው።

የሰው ልጅ መልካሙን የአዕምሮ ባህርይውን የሚያጣበት መንገድ ልክ በመጥረቢያ የሚቆረጥ ዛፍ ጋር የሚመሳሰል ነው። ዕለት ዕለት አስተሳሰብህን እንደዛፍ ቅርንጫፍ እየቆረጥህ ብትጥል ተፈጥሮአዊ ውበትህ እንደሚጠፋ ልብ ብለሃል?
ነገር ግን ቀንም ሆነ ማታ የተቆረጠ ዛፍ ከማቆጥቆጥ እንደማይቆጠብ ሁሉ እንዲሁ ደግሞ የሰው አዕምሮ ወደ ነበረበት ለመመለስ መፀፀቱና ማሰቡ አይቀርም።

ወዳጄ ሆይ… የአንተነትህ ምስል የአስተሳሰብህ ስዕል ነው፡፡ እይታህ የሚወለደው ከአመለካከትህ ነው፡፡ ምግባርህና ማንነትህ የሚታወቀው በስራህ ነው፡፡ ስራህ ደግሞ ተምጦ የሚወለደው ከሃሳብህ ነው፡፡ ሃሳብህ ከተበላሸ፣ የዘራኸው ከመከነ ፍሬህ አይጎመራም፡፡ መልካም አያያዝን አግኝቶ የማያድግ እንደሌለ ሁሉ በአያያዝ ጉድለትም እንዲሁ የማይበሰብስ ነገር የለም። አጥብቀህ የያዝከው ነገር ከአንተ ጋር ይኖራል፤ የለቀቅከው ደግሞ ሄዶ ይበሰብሳል፣ የአዕምሮህ መጥፎ ሀሳብ ካሸነፈ አንተንም ሆነ ሌሎችን ይመርዛል።

              ሰናይ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot