Get Mystery Box with random crypto!

#መልስ_ያላገኘው_ጥያቄ የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ባለፈው | Ethio Home Solutions

#መልስ_ያላገኘው_ጥያቄ
የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ባለፈው ሙሉ በሙሉ የተሰረዘው ዕጣ ሳይወጣ የእነሱ ጉዳይ ላይ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳሰቡ።
የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሰናል ብለው እየቆጠቡ ያሉ ወገኖች አለን ስላሏቸው ጥያቄዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማሳወቃችን አይዘነጋም።
" ዛሬም ድረስ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ የሚሰጠን አጥተናል " ያሉት ነዋሪዎቹ " ከልጆቻችን ምግብ ቀንሰን፣ በቤት ክራይ እየተሰቃየንና እየተማረርን ላለፉት 9 ዓመታት ቆጥበን ስለምን በዕጣው ልንካተት እንዳልቻልን በግልፅ ሊነገረን ይገባል " ብለዋል።
የቀጣዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከመውጣቱ በፊትም መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።
የ2005 ዓ/ም 20/80 ለባለ 3 መኝታ ቆጣቢዎቹ ፤ " #ቤቶቹ_የትገቡ ? ፣ #ተስፋ_አድርገን_ነበር ፤ #13ኛው_ዙር_ላይ_97_አልቋል_ብላችሁን_አልነበር?! ፤ #ባለ3_መኝታ_ኦዲት_ይደረግ ፤ #ፍትህ_እንሻለን! "በሚሉ እና በሌሎች ሀሽታጎች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ በመሰባሰብ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ዘመቻ እያካሄዱ መሆኑን ገልፀዋል።