Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/ ኮንክሪት ለመብ | Ethio Construction

የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል።

እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።

እነዚህም

1. Slump test
2.Compacting factor test
3.Veebee test እና
4.Vibro workability test ናቸው።

ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት /Slump test /Cone test/ or /Sand test/

የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም

2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/ :-ይህ ቅርፅ ማውጫ 30 cm
ቁመት የታችኛው ዲያሜትር 20 cm
የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

Plate/መደብ/ :- ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

ማስታወሻ

ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች /Results to be/

True Slump

ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

Zero Slump

ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

Collapsed Slump:

ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል እንዲሁም የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

Shear Slump

ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።


https://t.me/ethioengineers1