Get Mystery Box with random crypto!

Angle እና Direction . *Northing = ማለት Y-Coordinate ማለት ነው ከ (0 | Ethio Construction

Angle እና Direction
.
*Northing = ማለት Y-Coordinate ማለት ነው ከ (0,0) ወደ Y direction ምን ያህል እንደሚሄድ የሚያሳይ ነጥብ

*Easting = X Coordinate
*Azimuth angle =Clockwise አቅጣጫ
ከ North ስንለካ የምናገኘው አንግል

*Bearing = acute angle ሲሆን clockwise ወይም counterclockwise ከ
North ወይም South ስንለካ የምናገኘው

*ከዚህ ሌላ ህንፃዎች ላይ ከ angle እና direction አለማወቅ ወይም ግዴለሽነት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡

ለምሳሌ ለፀሀይ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ትልልቅ መስታወቶችን / መስኮቶችን ማድረግ፣ ዲዛይን ሲደረጉ ከታሰበላቸው አቅጣጫ ውጪ
የዞሩ ህንፃዎች መገንባት (በስህተት ፊታቸውን ወደ መንደር ጀርባቸውን ወደ መንገድ ያዞሩ
ሞሎች፣ መኖሪያ ቤቶች ወዘተዎች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን) ፣ ያልሆነ ቦታ ላይ ግንባታ በመጀመር ህንፃን ያልሆነ ቦታ ላይ
ማሳረፍ ወይም የሰው ይዞታ ውስጥ እስከመግባት ፣ ስራው ከተጀመረ በኋላ አቅጣጫው ልክ እንዳልሆነ ሲያውቁ ፓዶችን
እያነሱ ቦታ ማቀያየር ካልተቻለም እንደዛው የዞረ ፎቅ ገንብቶ መጨረስ …… ሁሉም
ከአቅጣጫ አለማወቅ የተነሳ የሚፈጠሩ ችግሮች ናቸው፡፡

North, East, South, West አለማወቅ የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ አልተማሩም የምንላቸው አባቶቻችን እናቶቻችንን ሲቀጥሩ
‹‹በስተምዕራብ በኩል ያለው ዛፍ ስር ጠብቂኝ›› ሲሉ እናቶቻችንም ‹‹የከሰዓቱ ፀሀይ እንዳያስቸግረን በስተሰሜን በኩል ያለው ዛፍ
ይሻለናል›› እያሉ ሃሳብ ያቀርቡ ነበር::

እኛ ፊደል ቀመሶች ግን ለስራ ደቡብ ክልል ተልከን
ሰሜን ምስራቅ ክልል እንገኛለን፡፡

*ለማንኛውም አቅጣጫን ለማወቅ 3 መንገዶች አሉ፡፡
.
*አንደኛ ኮምፓስ መግዛት ወይም ስልክህ ላይ የኮምፓስ አፕሊኬሽኖችን መጫን፡፡

*ሁለተኛ ጠዋትና ማታ የፀሀይ መግቢያና መውጪያ ቦታዎችን እያዩ አዕምሮአችን አቅጣጫዎቹን
ሴቭ እንዲያደርግ መጣር፡፡

*ሶስተኛው ደሞ ኮምፓስ ከሌለንና ፀሀይ እስክትገባ የምንጠብቅበትም ሰዓት ከሌለን ዞር ዞር በማለት ዲሽ መፈለግ… ናይልሳት የተሰራ ዲሽ ጀርባ በመሆን LNB የምትይዘዋ ዘንግ ቀጥታ የምታሳየው 7 ዲግሪ West ነው፡፡

ስለዚህ ከዲሹ አቅጣጫ በመነሳት ሌሎቹንም
አቅጣጫዎች ማወቅ ትችላለህ፡፡  

ደሞ ዲሽ አገኘው ብለህ በአረብ ሳት አቅጣጫ
ተመርተህ ወደ ሰማይ የዞረ ፎቅ እንዳትሰራ “ናይልሳት ነው seven degree West


https://t.me/ethioengineers1