Get Mystery Box with random crypto!

ከ ኢንጅነር አቤሴሎም መለስ Fm addis 97.1 Series 2000: Site Clearanc | Ethio Construction

ከ ኢንጅነር አቤሴሎም መለስ Fm addis 97.1

Series 2000: Site Clearance

ሳይቱ ለግንባታ  clear በሚደረግበት ሰአት ክሊር የተደረገውን area አጋኖ ማቅረብ
በ clearing ወቅት መፍረስ ያለበት ማንኛውም structure ካለ ስራውን አጋኖ ማቅረብ

Series 3000: Drainage Structure

የፍሳሽ ትቦዎች ሲሰሩ ቁፏሮውን፣ ግንባታውን፣ back fill ኡንም ጭምር quality ማሳነስ ... ክፍያ ላይ ግን quantity አጋኖ ማቅረብ
መንገዱን አቋርጠው የሚሄዱ ትቦዎች ( cross drainage ወይም culvert) በሚሰሩበት ጊዜ ቁፏሮ፣ backfill ፣ ግንባታውን ወዘተ quality ማሳነስና እንደነገሩ መስራት ... ክፍያ ላይ ያው የተዋዋልነው ተሰርቷል ማለት
የድንጋይ ስራዎች stone pitching፣ masonry ፣ riprap ወዘተ ስራዎችን ማጋነን
ለድልድይና ለትቦዎች ደህንነት የሚሰሩ ግንባታዎችን ማጋነን

Series 4000: Earthworks and Material Stabilisation

Road bed (( ወይም የመንገዱ የመጀመሪያው ንጣፍ ማለት ይቻላል)) ሲሰራ መጀመሪያ የነበረው ጥሩ ያልሆነ አፈር (unsuitable material) ተነስቶ ሌላ ተተክቷል ይባላል ((እውነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል)) ለዚህም ክፍያ አለው ... ቀጥሎም Road bed ለተሰራበት ይከፈላል ... የተሰራው መጠንና ካሊቲውን ፈጣሪ ያውቃል

ሌላው የመንገዱ ትልቁና ዋናው ወጪ Cut  እና Fill ነው ።
Cut section ሲኖር የተቆረጠውን volume አጋኖ ሪፖርት ማድረግ በተጨማሪም በቀላሉ የሚቆረጥ ወይም soft excavation ሆኖ ሳለ Hard Excavation ነው ብሎ ማስገባት ... ብሩ ይጨምራላ
Fill section ሲሆን ደሞ ያው በጥራትም ይሁን በ volume ብዙ መብላት ይቻላል። በተጨማሪ ደሞ fill ሲደረግ በ Layer ነው የሚሞላው ለምሳሌ በ25 ሳንቲም thickness ትሞላለህ ከዛ ኮምፖክት ታደርጋለህ ከዛ ክፍያ ይሰጥሃል ... ሳይት ላይ ምን ሊደረግ ይችላል መሠለህ?? ... 1 ሜትር ለመሙላት ኮንትራቱ ላይ በ25 እየተሞላ ይጠቅጠቅ ካለ 4 Layer ይኖራል ማለት ነው። 4x25 cm = 1 ሜትር ...ሳይት ላይ ግን በ2 layer ብቻ ሊሞላ ይችላል። በ50 cm ውፍረት ማለት ነው። ኮንትራክተሩ አራቴ ሰርቶ ሊያገኝ የሚገባውን በሁለት ስራ ያገኛል ማለት ነው። በዛ ላይ ከሙሉ ወጪው በግማሽ ይድናል። ለ50 ብር ስራውም 100 ይከፈለዋል።

Borrow area ለማግኘትም የተወሰኑ ንግግሮች ይኖራሉ በመሬቱ ባለ ይዞታዎችና በመንገዱ ባለቤት መሀል

Series 5000 : Sub Base, Road Base and Gravel Wearing Course

እዚህም እንደላይኛው volume በማምታታት ወይም layer በመቀሸብ ... Layer ቅሸባ ከሚገመተው በላይ አዋጭ ነው

Series 6000 - Bituminous Surfacings and Road Base

እዚህም እንደሌሎቹ volume ና layer ቅሸባ ነው።

Series 8000 - Structure

እዚህ ስር ያሉት masonry work , bridges, box and slab culvert, cofferdam, timber structures, structural steelwork ወዘተ ናቸው። እንደሚታወቀው እነዚህን ለመስራት የሚያስፈልጉት ማቴሪያሎች ፌሮ ፣ ሲሚንቶ ፣ aggregate ፣formwork ያስፈልጋል። excavation እና backfill ስራዎች ይኖራሉ .... በሌባ አእምሮ do the maths!

Series 9000 - Ancillary Work

በእዚህ ስር ያሉት gabion, mattresses, kilometer የሚያመላክቱ ኮንክሪቶች ( Kilometer Post), አስፖልቱ ላይ የሚቀቡ ቀለሞች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ guardrail ፣ ከግንባታ በኋላ አካባቢውንና borrow areaውን ወደ ተፈጥሯዊው ሁኔታ ለመመለስ የሚሰሩ ማስተካከያዎችና የእፅዋት ተከላዎች ፣ አጥሮች ፣ የእግረኛ መንገዶች ፣ ለሴፍቲ ተብለው የሚሰሩ የኮንክሪትና masonry ግድግዳዎች ወዘተ ናቸው።

መንገድ ስራ ላይ ማጭበርበርና ውሸት እንደ hobby ወይም ዝንባሌ ነው። ጥዋት ተነስተህ እስፖርት እንደምትሰራው ምናምን በቃ የመንገድ ስራ ሰራተኞች ወደዛ ያዘነብላሉ። በተለይም ከአዲስ አበባ የራቀ ቦታ ላይ ከሆነ ሌቦቹ እንደፈለጉ ይፈነጩብሃል። መንግስት የለም ወይ የሚያስብለኝ ከህዝቦች መሞት ይልቅ መንገድ ስራ ላይ የሚሠራውን ሳይ ነው። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩ እንደአለቃ ይሆንብሃል። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩን ብታማ እንዳንተው ተቆጣጣሪ ተብሎ የተሾመው አለቃህ ይገላምጥሀል ፣ ይነዘንዝሃል። ለምን ካልክ ብዙ ሴራዎችን እየሠሩ መሮህ እንድትሄድ ያደርጉሀል። ይሄንን ፅሁፍ የፃፍኩት ስርቆቱ በግልፅ እንዲታወቅና መፍትሄ እንዲሰጠው ነው። ነገሮቹ መዘርዘራቸውም ለእያንዳንዱ ችግር የራሳችሁን መፍትሄ እንድታስቡ ነው።

የተሻለ መፍትሄ ካላችሁ ወዲህ በሉ
...........

መፍትሔው ምንድነው??

1. የመንገድ ባለቤቶች የራሳቸውንም ሰራተኛ፣ ኮንሰልታንቱንም ይሁን ኮንትራክተሮችን ማመን የለባቸውም። ከዚህ ሰርክል ወጣ እያሉ ስራዎችን ቼክ ማድረግ።
2. የተለያዩ ምርምሮችን በማሰራት አዳዲስ የአሰራርና የቁጥጥር መንገዶችን መፍጠር
3. የሚያጋልጡ ግለሰቦችን ማበረታታት
4. መንገድ ስራ ላይ በአብዛኛው በሰርተፍኬት/ዲፕሎማ ነው የሚሰሩት። እነዚህም ሰዎች ስራ እናጣለን በሚል ስጋት የተባሉትን አሜን ብለው ነው የሚሰሩት። የተማረውን ማስገባት የተሻለ ነው።
5. የመንገዶች ባለቤቶች የተቆጣጣሪውንና የራሳቸውን ሰራተኞች ደሞዝ ቢጨምሩ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሰዋል።


https://t.me/ethioengineers1