Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአለም አቀፍ የ | Ethio Construction

ማስታወቂያ

ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአለም አቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎችን የገበያ ድርሻ የሚያሳይ መረጃ ለማደራጀትና የቀጣይ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚስችሉ መረጃዎችን በማደራጀት ላይ ይገኛል፡፡
የሀገርበቀል አለም አቀፍ ተጫራቾች መረጃ በተደራጀ መልኩ  ተመዝግበው መደራጀታቸው በቀጣይ እንደሀገር ለሚኖረው እንቅስቃሴ  ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ  ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ባለድርሻዎች መረጃዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ይጠይቃል፡፡
1. በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ፕሮጀክቶቻቸው የታየ ወይም እየታየ ያሉ ኩባንያዎች
2. በዓለም ዓቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የተወዳደሩ ወይም ያሸነፉ ኩባንያዎች
3. በአህጉር ደረጃ በሚወጣ ጨረታ (ICB) እና ተያያዥ ውሎች ላይ የተሳተፉ የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎች በሙሉ አዋሬ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋናው መስሪያ ቤት 6ኛ
ፎቅ ሀገር አቀፍ የኮንስትራክሽን መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ እንድታስመዘግቡ እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ  0911409508


https://t.me/ethioengineers1