Get Mystery Box with random crypto!

የቤት እድለኞች ለመዋዋል በወጣላቸው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ካልተዋዋሉ ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆ | Ethio Construction

የቤት እድለኞች ለመዋዋል በወጣላቸው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ካልተዋዋሉ ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ለመንግስት ተመላሽ ይሆናል ተባለ።

የቤቶች ኮርፓሬሽን በ20/80 ለ14ኛ ዙር ፣ በ40/60 ለ3ኛ  ዙር የጋራ መኖሪያቤት አጣ ወጥቶላቸው  ውል እንዲዋዋሉ ከጥር 1/2015 ዓ.ም.  ጀምሮ ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት ቅፅ 09 ወደ መኖሪያ ቀበሌዎች ወስደው አስሞልተው ለማምጣት ቀርበው የወሰዱ 23,813 ሲሆኑ የቀበሌውን ቅፅ 9 አስሞልተው በመመለስ ቅፅ 03 ወደ ባንክ ቀርበው የወሰዱት ሰዎች ብዛት 11,865 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የባንኩን ሂደት ጨርሰው ወደ አንድ ማእከል ተመልሰው እስከ የካቲት 18/2015 ዓ,ም. ድረስ ውል የተዋዋሉ 9,568 ሰዎች ሲሆኑ የባንኩን ቅፅ 03 ወስደው እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ ደግሞ 2,297 ሰዎች ናቸው ።

ከጥር 1 እስከ የካቲት 18/2015 ዓም ድረስ አስፈላጊውን ፕሮሰስ ጨርሰው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰራላቸው የተላኩ 8,416  ሰዎች ብቻ መሆናቸውን የኮርፓሬሽኑ አስታውቀዋል ።

በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች ከ25,773 ሰዎች ውላቸውን ተዋውለው ካርታቸውን ሊወስዱ እንደሚገባ ካለው ቁጥር አንፃር ግን እስካሁን ውል የጨረሱት ሲታይ ገና ብዙ እንደሚጠበቅ እና ሰውጋ መዘናጋት እንደሚታይ ታውቋል።

የቤት እድለኞች በመመሪያችን መሰረት በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት እና ለመዋዋል በወጣላቸው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ካልተዋዋሉ ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ለመንግስት ተመላሽ ስለሚሆን ባለ እድለኞች አሁንም ወደ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት እንዲዋዋሉ ጥሪ አቅርበዋል


https://t.me/ethioengineers1