Get Mystery Box with random crypto!

#Tip #Motivation #Detailed ሰዎች ብዙ ጊዜ 'ተስፋ ቆረጥኩ' ወይም 'ተስፋ ል | ኢትዮ - ጂምናዚየም

#Tip
#Motivation
#Detailed


ሰዎች ብዙ ጊዜ "ተስፋ ቆረጥኩ" ወይም "ተስፋ ልቆርጥ ትንሽ ነው የቀረኝ" ይላሉ።

ለዚህ ምክንያት ብዙ ሊኖር ይችላል።
በኔ ሀሳብ ግን ዋነኛው ምክንያት፡ ስፖርት ለምን መስራት እንደጀመርን መርሳት ወይም ያለ ምክንያት እና ያለ እቅድ መጀመራችን ነው ብዬ አስባለው።

ስፖርት ለመጀመር ከተለመዱት ምክንያቶች ውስጥ፡ ውፍረት ለመቀነስ፡ ጡንቻ ለማውጣት፡ ለጤንነት፡ የመሳስሉት ናቸው።

አንዳንዱ ደግሞ፡ ጓደኛዬ ሲሰራ አይቼው ነው፡ ስፖርት አሪፍ ነው ሲሉ ሰምቼ ነው፡ ሁሉም ሰው ውፍረት ቀንሺ ብለውኝ ነው የጀመርኩት የሚሉም አሉ። ብዙ ጊዜ ምክንያታቸው እነዚህ ከሆኑ የማቆም እና የመሰላቸታቸው መጠን ከፍ ያለ ነው። እነዚህ ስዎች ተስፋ ቆረጥን ለማለት መብት የላቸውም፡ ምክንያቱም ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ሲጀመር #አላማ ያለው ሰው፡ አላማውን ማሳካት ሲከብደው ነው።

ሌላኛው እና ብዙ ጊዜ የማናስተውለው ነገር፡
ስፖርት የምናሳካው ነገር ሳይሆን #የኑሮ_ዘይቤያችን ነው መሆን ያለበት። ብዙ ጊዜ ካስተዋላችሁት፡ ጠዋት ጠዋት የሚሮጡ ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው። ሁልጊዜ የሚሮጡ እና አንዳንድ ጊዜ ብቅ ጥፍት የሚሉ ናቸው። ልዩነታቸው አንደኛው እራሱን ሯጭ ነኝ ብሎ ስለሚያምን ሁል ጊዜ ይሮጣል፡ ሌላኛው ደግሞ ሌሎች ሲሮጡ አይቶ የሆነ ቀን ሞራሉ ይመጣና ይሞክረዋል፡ ትንሽ ቀን ይሮጥና ይሰለቸዋል፡

የቱም አይነት የምንሰራው ስፖርት እና እቅዳችን ቢለያይም፡ ውፍረት መቀነስም ይሁን፡ ጡንቻ ማውጣትም ይሁን፡ አተነፋፈሳችንን ለማስተካከልም ይሁን፡ #አላማችን ስፖርተኛ መሆን ከሆነ አና #የኑሮዋችን ዘይቤ ካደረግነው ወጤታችን ምንም ይሁን ምን መስራታችንን አናቆምም።

የጀመርንበትን ምክንያት በትክክል ማስታወስ ይኖርብናል። #ወፍረት አሰቃይቶን የጀመርን አለን፡ #ቅጥነታችን ያሸማቀቀን ይኖራል፡ #ጤንነታችን አደጋላይ ሆኖብን የጀመርን ብዙ አለን፡ አትችሉም ያሉንም አሉ። ሁሌ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲሰማችሁ፡ መጀመርያ ለምን እንደጀመርን ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው። በጣም ይጠቅመናል።


የመጨረሻው ደግሞ ባለፈው እንዳልነው፡ ከአፋችን የምናወጣው ቃላት ላይ እንጠንቀቅ። በተደጋጋሚ የምንናገረውን ነው የምንሆነው።
"ተሰፋ ልቆርጥ ነው" በተደጋጋሚ ካልነው አትጠራጠሩ ተስፋ እንቆርጣለን። በተመሳሳይ ጭራሽ ከአፋችን ማናወጣው ከሆነ እና "ምንም ቢፈጠር ወደኋላ አልልም፡ የመጣው ይምጣ፡ ምንም ጊዜ ይፍጅ፡ ያሰብኩትን ከማሳካት ምንም አያስቆመኝም" የምንል ከሆነ ደግሞ እውነትም ማንም፡ ምንም ሊያስቆመን አይችልም።