Get Mystery Box with random crypto!

እረኛዬ! የኢትዮጵያችንን ጠቧንና ፍቅሯን፣ ለቅሶዋንና ሳቋን፣ የኋላዋንና የፊቷን፣ ስህተቷንና እ | ታሪካዊት ኢትዮጵያ (History of Ethiopia )

እረኛዬ!

የኢትዮጵያችንን ጠቧንና ፍቅሯን፣ ለቅሶዋንና ሳቋን፣ የኋላዋንና የፊቷን፣ ስህተቷንና እርማቷን፣ ጨለማዋንና ብርሃኗን፣ ፍርሃቷንና ድፍረቷን፣ ሃዘኗንና ደስታዋን፣ ድካሟንና ብርታቷን፣ ጥፋቷንና ልማቷን፣ ውሸቷንና እውነቷን፣ ደዌዋንና ፈውሷን፣ ስብራቷንና ጥገናዋን፣ መካንነቷንና ወላድነቷን፣ መርገሟንና በረከቷን፣ ስቃይዋንና ፍሰሃዋን፣ ወከባዋንና እረፍቷን፣ ስቃይዋንና ሰላሟን፣ ድህነቷንና ባለጸግነቷን፣ በደሏንና ምህረቷን፣ ጥርጣሬዋንና እምነቷን፣ ቁዘማዋንና ሃሴቷን፣ መውደቅና መነሳቷን፣ ጠላቷንና ወዳጇን፣ ቂሟንና ይቅርታዋን፤ ማጣቷንና ማግኘቷን፣ ሞቷንና ትንሳኤዋን ቁልጭ አድርጎ አሳየን! ፍቅር ከጥላቻ፣ ምህረት ከህይወት፣ ይቅርታ ከቂም፣ ብርሃን ከጨለማ፣ በደልን መሸፈን ከበቀል ምን ያህል አብልጠው ሃያልና አሸናፊ እንደሆኑ በእረኛዬ ግዙፍ የተስፋ መስኮት ውስጥ ይታያሉ!

ድርሰቱ ለሃገር መርህ ሊሆን የሚችል፣ መልዕክቱ በልቦና ቢያድር ሃገር የሚዋጅ፣ ሃሳቡ ቢተገበር ትውልድ የሚያድን፣ ትወናው እንደ ጥበብ ጥግ ተቆጥሮ ሁሌም የሚሞገስ፣ ደራሲያኑ፣ ተዋንያኑ፣ የሙዚቃና የፊልም ባለሞያዎቹም ክብር የሚያሰጣቸው ብቻ ሳይሆን የሃገር ጀግኖች የሚያስብላቸው ነው!

እረኛዬ — የኢትዮጵያ የመዋጀት ተስፋ መስኮት!

Great job Arts Tv World!

( ሰሎሞን ሙሉጌታ ካሳ (tech talk with Solomon )
https://youtube.com/channel/UCJxIzBiXCY8chIBzfyAGtIA

@ethioabesha @ethioabesha @ethioabesha