Get Mystery Box with random crypto!

ድሮ በልጅነት መስከረም 30 ሆነ ግንቦት 30 የተጣላ ' #ሰኔ_30_እንገናኝ !'ይል ነበር ምክንያ | ታሪካዊት ኢትዮጵያ (History of Ethiopia )

ድሮ በልጅነት መስከረም 30 ሆነ ግንቦት 30 የተጣላ " #ሰኔ_30_እንገናኝ !"ይል ነበር ምክንያቱም ትምህርት ይዘጋላ ተደባደባችሁ ተብሎ ወላጅ መጥራት የለም በዛ ላይ ለተፈራራም ለግዜው ድብድቡን በቀጠሮ በማራዘም እፎይታ
ማግኛ መንገድ ነው። ሰኔ 30 እንገናኝ ሲባል አይ ዛሬውኑ ይዋጣልን ' የሚል
የለም። ከዛ ምስኪን የልጅነት ዘመን የምንማረው ትልቅ ነገር ቢኖር
ከተቀጣጠረው ውስጥ ምን ያህሉ የእውነት ይደባደባል ? በጣም ጥቂቱ ብቻ
ነው ! ልጅነት ቂመኛ አይደለም።
በዛ የዋህ ልባችን አብዛኞቹ ጥሎች ከሰኔ ሰላሳ በፊት ተረስተው ይቀራሉ።
ኤለመንታሪ እያለሁ ብዙ ድብደባዎች ደርሰውብኛል። እልሀኛ ስለነበርኩ
ከምችለውም ከማልችለውም ጋር እደባደባለው።አንድ የማስታውሰው ገጠመኝ
ግን ከክላሳችን ጉልቤ ጋር ኩዋስ ሜዳ ላይ የተጣላሁት ነው። ጎል ገባ አልገባም
ስንጨቃጨቅ ገፍትሮ አስወጣኝ። ለዛውም ሁሉም የክላስ ልጅ ባለበት ገፍትሮ ጣለኝ።
በሆዴ እያብሰለሰልኩ ወደ ቤቴ አመራሁ።
ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ልወጣ ስል ግድግዳ ላይ የተሰቀለው ካሌንደር ላይ
አይኔ አረፈ።ሰኔ ሰላሳን ፈልኩዋት አገኘሁዋት ፈገግ አልኩ።
በእረፍት ሰአት እንደለመድነው ካስ ስንጫወት ጉልቤው እየበረር ሲሮጥ ሆን ብዬ
ጠለፍኩት ክፉኛ ወደቀ ከወደቀበትም ተነስቶ ያዘኝ ቆፍጠን ብዬ
"ልቀቀኝ! ከፈለክ ሰኔ 30 እንገናኝ !.አሁን ተደባድቤ ወላጅ ማምጣት አልፈልግም"አልኩ
ማንም ያልኩትን አላመነም ሁሉም ደንግጠዋል
"እሺ ! አፈራርጥሃለሁ" አለኝ " እናያለን ! "አልኩት አሁን ፈሪ እንዳልሆንኩ ተማሪዎቹ ያመኑ ትመስላለች።የሚፈለገውም ይህ ነው።
ይቺ የድፍረት ቀጠሮዬ ከብዙ እኩዮቸ ጋር አከባበረችኝ። ምን አስጨነቀኝ
እስከዛ ይረሳሳልኛል።ካልተረሳም አይጨንቀኝም ሰኔ 30 እሁድ ቀን እንደሚውል
ካላንደሩ ላይ አይቻለሁ የታባቱ ያገኘኛል ?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

https://youtube.com/channel/UCJxIzBiXCY8chIBzfyAGtIA

@ethioabesha @ethioabesha