Get Mystery Box with random crypto!

በቅርቡ የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስት | Ethio telecom

በቅርቡ የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቦርዱ አባላት ጋር በመሆን በኩባንያችን የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ጉብኝት አደረጉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቦርድ አባላቱ ጉብኝታቸውን በአድዋ የድል መታሰቢያ በሚገኘው የኩባንያችን ኤክስፒሪየንስ ማዕከል በመጀመር በፕሪሚየም አገልግሎት ማዕከል፣ ሞጁላር ዳታ ሴንተር እና የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ኩባንያችን የኮኔክቲቪቲ ተደራሽነት እና ጥራት ከማሻሻል ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽኖችን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ የህዝባችንን ህይወት ለማቅለል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በቴሌኮም እና በዲጂታል መሠረተ ልማት አቅም የተፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም የመንግስት ተቋማት አሰራሮቻቸውን በዲጂታል በማዘመን ፈጣን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ የተገነቡ የዲጂታል አቅሞችን እንዲያውቁት እና እንዲጠቀሙበት ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ዕውን ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት እና አስተዋጽኦ በማድነቅ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቦርዱ ተገቢውን ድጋፍ እና አመራር እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia