Get Mystery Box with random crypto!

እድለኛዋ ወጣት ከዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እጅ አውቶሞቢሏን ተረከበች! ጥሪ ማሳመሪያ ጥሪት ያተር | Ethio telecom

እድለኛዋ ወጣት ከዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እጅ አውቶሞቢሏን ተረከበች!


ጥሪ ማሳመሪያ ጥሪት ያተርፋል! ብለን በእውን ጥሪት አትራፊ እድለኛ ደንበኞቻችንን ያንበሸበሽንበት ፕሮግራም የመኪና እድለኛ ከወለጋ ኪረሙዋ ወጣት ዘይነባ ፋንታሁን የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ቁልፏን ከዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ እጅ ተረክባለች፡፡

በተመሳሳይም የጅማ አላጌዋ ዕድለኛ ቢሊሴ ደነቀ ደግሞ የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዋን ተረክባለች፡፡

ከጥቅምት 26 - ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለደንበኞች ባዘጋጀነው ልዩ የጥሪ ማሳመሪያ ሽልማት መርሃግብር ለደብረታቦር፣ ጎጃም ዘግዛ እና ቢሾፍቱ እድለኞች ለእያንዳንዳቸው የባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ቁልፍ ማስረከባችንን የሚታወስ ሲሆን 8 ስማርት ቴሌቪዥን፣ 8 የ5ጂ ስማርት ስልኮች፣ 80 የ5 ሺህ ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ እና ከ13 ሺህ በላይ የሞባይል ጥቅሎች አበርክተናል፡፡

በቅርብ ቀን የውድ ደንበኞቻችንን አኗኗር እና ምቾት በሚጨምሩ አዳዲስ አገልግሎቶቻችን እና እጅግ አጓጊ ሽልማቶች በሚያስገኙ የተለያዩ መርሀ ግብሮች ይጠብቁን!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia